Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 20:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በቤትመዓካ ባለ በአቤልም መጥተው ከበቡት፥ በከተማይቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፥ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ይደባደቡ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከኢዮአብ ጋራ ያለውም ሰራዊት መጥቶ፣ ሳቤዔን በአቤል ቤትመዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኀይል በሚደበድቡበት ጊዜ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከኢዮአብ ጋር ያለውም ሠራዊት መጥቶ ሼባዕን በአቤል ቤት መዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኃይል ይደበድቡት ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የኢዮአብ ወታደሮች ሼባዕ እዚያ መሆኑን ስለ ሰሙ ሄደው ከተማይቱን ከበቡ፤ በስተውጪ በኩል ቅጽሩን አስደግፈው የዐፈር ቊልል ሠሩ፤ ቀጥሎም ቅጽሩ እንዲወድቅ ከስሩ መቈፈር ጀመሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በቤተ ማካና በአ​ቤ​ልም መጥ​ተው ከበ​ቡት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ላይ እስከ ቅጥ​ርዋ ድረስ የአ​ፈ​ርን ድል​ድል ደለ​ደሉ፤ እነ​ር​ሱም ከአ​ጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥ​ሩ​ንም ያፈ​ርሱ ዘንድ ከኢ​ዮ​አብ ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ተስ​ማሙ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 20:15
11 交叉引用  

እርሱ ግን ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ አቤል፥ ወደ ቤትመዓካ፥ ወደ ቤሪም ሁሉ አለፈ፥ ሰዎችም ደግሞ ተሰብስበው ተከተሉት።


ቤንሀዳድም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልቤት መዓካንና ኪኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም አገር ሁሉ መታ።


በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጥቶ ዒዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምን አገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሦርም አፈለሳቸው።


ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል “ወደዚች ከተማ አይመጣም፤ ፍላጻንም አይወረውርባትም፤ በጋሻም አይመጣባትም፤ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።


ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፥ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት።


ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።


እነሆ የአፈር ድልድል፥ ሊይዙአትም እስከ ከተማይቱ ድረስ ቀርበዋል፥ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም የተነሣ ከተማይቱ ለሚዋጉአት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች፥ የተናገርኸውም ሆኖአል፥ እነሆም፥ አንተ ታየዋለህ።


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ አፈርን ደልድሉ፥ ይህች ከተማ የምትቀሠፍ ናት፥ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


ምሽግም ሥራባት፥ አፈርም ደልድልባት፥ ሰፈርም አቁምባት፥ በዙሪያዋም የሚያፈርስ ግንድ አድርግባት።


ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤


跟着我们:

广告


广告