2 ሳሙኤል 20:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እንዲህም ሆነ፥ አንድ ብንያማዊ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የሚባል ምናምንቴ ሰው ነበረ፥ እርሱም፦ ከዳዊት ዘንድ እድል ፈንታ የለንም፥ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ ብሎ ቀንደ መለከት ነፋ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ምናምንቴ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በዚያም አንድ ብንያማዊ የቢኮሪ ልጅ ስሙ ሳቡሄ የሚባል የዐመፅ ልጅ የሆነ ሰው ነበረ፤ እርሱም፥ “ከዳዊት ዘንድ እድል ፋንታ የለንም፦ ከእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፥ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ” ብሎ መለከት ነፋ። 参见章节 |