Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በገለዓድና በአሹራውያን በኢይዝራኤልም በኤፍሬምም በብንያምም በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሠው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱንም በገለዓድ፣ በአሴር፣ በኢይዝራኤል፣ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱንም በገለዓድ ላይ፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ አነገሠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በገ​ለ​ዓ​ድና በታ​ሲሪ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም፥ በብ​ን​ያ​ምም፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ አነ​ገ​ሠው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 2:9
19 交叉引用  

ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።


የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴም በእስራኤል ላይ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአርባ ዓመት ሰው ነበረ፥ ሁለት ዓመትም ነገሠ፥ ነገር ግን የይሁዳ ቤት ዳዊትን ተከተለ።


በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ጦርነት ሆኖ ሳለ አበኔር በሳኦል ቤት ይበረታ ነበር።


የሳኦልም ወንድሞች ከሆኑ ከብንያም ልጆች የሚበልጠው ክፍል እስከዚያ ዘመን ድረስ የሳኦልን ቤት ይከተል ነበርና ከእነርሱ ዘንድ የመጡ ሦስት ሺህ ነበሩ።


ጽኑዓን፥ ኀያልን የሆኑ በአባቶቻቸውም ቤት የታወቁ የኤፍሬም ልጆች ሃያ ሺህ ስምንት መቶ ነበሩ።


የአሴር ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥


የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፥ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፥


ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።


ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር፥ ነው።


ለምናሴ ነገድ ዕጣ ይህ ነው፥ የዮሴፍ በኩር እርሱ ነውና። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ብርቱ ሰልፈኛ ስለ ነበረ ገለዓድንና ባሳንን ወረሰ።


የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፥ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ።


በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙርያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ።


ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥


የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፥ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።


በዚያችም ምድር የተቀመጡትን ከነዓናውያን አላወጡአቸውምና በመካከላቸው የአሴር ልጆች ተቀመጡ።


ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፥ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።


跟着我们:

广告


广告