Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአልና እጃችሁ ትጽና፥ እናንተም ጨክኑ፥ ዳግም የይሁዳ ቤት በእነርሱ ላይ ንጉሥ እሆን ዘንድ ቀብተውኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንግዲህ ጠንክሩ፤ በርቱ፤ ጌታችሁ ሳኦል ሞቷልና፤ የይሁዳ ቤትም እኔን ቀብተው በላያቸው አንግሠውኛል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንግዲህ ጠንክሩ፤ በርቱ ጌታችሁ ሳኦል ሞቷልና፤ የይሁዳ ቤትም እኔን ቀብተው በላያቸው አንግሠውኛል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንግዲህ ጠንክሩ! በርቱም! ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአል፤ የይሁዳ ሕዝብ እኔን ቀብቶ አንግሦኛል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም ጌታ​ችሁ ሳኦል ሞቶ​አ​ልና እጃ​ችሁ ትጽና፤ እና​ን​ተም በርቱ፤ የይ​ሁ​ዳም ቤት በእ​ነ​ርሱ ላይ ንጉሥ እሆን ዘንድ ቀብ​ተ​ው​ኛል።”

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 2:7
12 交叉引用  

ከዚህ ነገር በኍላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፤ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


አይዞህ፥ ስለ ሕዝቦችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፥ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ።


አሁንም እግዚአብሔር ቸርነትንና እውነትን ያድርግላችሁ፥ ይህንም ነገር አድርጋችኋልና እኔ ደግሞ ይህን ቸርነት እመልስላችኋለሁ።


የሳኦልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበኔር የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፥


የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፥ ንጉሡ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አደረገ፥ በእስራኤልም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን ቀቡት።


የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብተውም ንጉሥ አደረጉትና “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ እጃቸውን አጨበጨቡ።


የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። እጃቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።


ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።


በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።


ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ የሳኦልንም ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ከቤትሳን ቅጥር ላይ አወረዱ፥ ወደ ኢያቢስም መጡ፥ በዚያም አቃጠሉት።


በሸለቆውም ማዶና በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያን የእስራኤል ሰዎች እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተማቹን ለቅቀው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።


እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፥ አይዞአችሁ፥ ጎብዙ፥ እናንተ ባሪያዎች እንዳደረጋችኋቸው ዕብራውያን ባሪያዎች እንዳያደርጉአችሁ ጎብዙ፥ ተዋጉ።


跟着我们:

广告


广告