Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አበኔርም አሣሄልን፦ ከምድር ጋር እንዳላጣብቅህ እኔን ከማሳደዱ ፈቀቅ በል፥ ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ፊቴን አቅንቼ አይ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እንደ ገናም አበኔር አሣሄልን፣ “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋራ ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንደገናም አበኔር፥ “እኔን ማሳደድህን ተው! እኔስ ስለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንደገናም አበኔር “እኔን ማሳደድህን ተው! ለምን እንድገድልህ ትገፋፋኛለህ? አንተንስ ብገድል የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ማየት እችላለሁ?” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አበ​ኔ​ርም አሣ​ሄ​ልን፥ “ከም​ድር ጋር እን​ዳ​ላ​ጣ​ብ​ቅህ እኔን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ በል፤ ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ፊቴን አቅ​ንቼ አይ ዘንድ እን​ዴት ይቻ​ለ​ኛል? እን​ደ​ዚህ አይ​ሆ​ን​ምና ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ተመ​ለስ” አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 2:22
6 交叉引用  

አበኔርም፦ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፥ አንድ ጕልማሳ ያዝ፥ መሣርያውንም ውስድ አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቆይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፥ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ሆዱን መታው፥ ሞተም።


የሆነውም ስሙ አስቀድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፥ ከእርሱ ከሚበረታው ጋር ይፋረድ ዘንድ አይችልም።


ሳኦልም ሜልኮልን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገሽ አታለልሽኝ? ጠላቴን አስኮበለልሽው አላት። ሜልኮልም ለሳኦል፦ እርሱ፦ አውጥተሽ ስደጂኝ፥ አለዚያም እገድልሻለሁ አለኝ ብላ መለሰችለት።


跟着我们:

广告


广告