Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 19:42 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች መልሰው፦ ንጉሡ ለእኛ ቅርባችን ነው፥ ስለ ምን በዚህ ነገር ትቆጣላችሁ? በውኑ ከንጉሡ አንዳች በልተናልን? ወይስ እርሱ በረከት ሰጥቶናልን? አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፣ ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለ ሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቈጣ ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሏቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው፥ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን በሹልክታ ለብቻቸው ይዘው እርሱንና ቤተሰቡን ከተከታዮቹ ጋር ዮርዳኖስን ለምን አሻገሩ?” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 የይሁዳም ሰዎች “እኛ ይህን ያደረግነው ንጉሡ የእኛ ወገን ስለ ሆነ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ እናንተስ በዚህ ነገር ስለምን ትቈጣላችሁ? እርሱ ለምግባችን ምንም የከፈለን ነገር የለም፤ ሌላም ምንም ነገር አልሰጠንም” ሲሉ መለሱላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች መል​ሰው፥ “ንጉሡ ለእኛ ቅር​ባ​ችን ነው፤ ስለ​ምን በዚህ ነገር ትቈ​ጣ​ላ​ችሁ? በውኑ ከን​ጉሡ አን​ዳች በል​ተ​ና​ልን? ወይስ እርሱ በረ​ከት ሰጥ​ቶ​ና​ልን? ወይስ ጭፍራ አድ​ርጎ ሾመ​ንን?” አሉ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 19:42
6 交叉引用  

እናንተ ወንድሞቼ፥ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ ናችሁ፥ እናንተ ንጉሡን ከመመለስ ስለ ምን ዘገያችሁ?


የእስራኤልም ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች መልሰው፦ በንጉሡ ዘንድ ለእኛ አሥር ክፍል አለን፥ በዳዊትም ዘንድ ደግሞ ከእናንተ ይልቅ መብት አለን፥ ስለ ምን ናቃችሁን? ስለ ምንስ ንጉሣችንን ለመመለስ ቀድሞ ምክር አልጠየቃችሁንም? አሉ። የይሁዳም ሰዎች ቃል ከእስራኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነከረ።


የይሁዳም ሰዎች መጥተው በይሁዳ ቤት ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን በዚያ ቀቡት።


የእስራኤልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው፦ እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን።


የኤፍሬም ሰዎች፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ምድያምን ለመዋጋት በወጣህ ጊዜ ለምን አልጠራኸንም? አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣሉት።


跟着我们:

广告


广告