Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 19:38 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ንጉሡም፦ ከመዓም ከእኔ ጋር ይለፍ፥ ደስ የሚያሰኝህንም አደርግለታለሁ፥ አንተም ከእኔ የምትሻውን ሁሉ አደርግልሃለሁ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ንጉሡም፣ “ከመዓም ከእኔ ጋራ ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በገዛ ከተማዬ ሞቼ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እንድቀበር፥ እባክህ፥ አገልጋይህን አሰናብተውና ይመለስ፤ ነገር ግን አገልጋይህ ኪምሃም እነሆ፤ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይሻገር፤ ደስ ያለህንም ነገር አድርግለት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ንጉሡም “እርሱን ይዤ እሄዳለሁ፤ እንዳደርግለት የምትፈልገውንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ለአንተም ቢሆን የምትጠይቀውን ሁሉ እፈጽማለሁ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ንጉ​ሡም፥ “ከመ​ዓም ከእኔ ጋር ይሻ​ገር፤ በፊቴ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ከእኔ የም​ት​ሻ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 19:38
4 交叉引用  

እኔ ባሪያህ ተመልሼ በከተማዬ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ፥ እባክህ፥ ልሙት። ነገር ግን ባሪያህን ከመዓምን እይ፥ እርሱ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይለፍ፥ ደስ የሚያሰኝህንም ለእርሱ አድርግ።


ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፥ ንጉሡም ተሻገረ፥ ንጉሡም ቤርዜሊን ሳመው፥ መረቀውም፥ ወደ ስፍራውም ተመለሰ።


ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች መልካም ቸርነት አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ።


ተነሥተውም ወደ ግብጽ ይሄዱ ዘንድ በቤተልሔም አጠገብ ባለው በጌሮት ከመዓም ተቀመጡ፥


跟着我们:

广告


广告