2 ሳሙኤል 18:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ኢዮአብን፦ የሆነ ሆኖ ኵሲን ተከትዬ፥ እባክህ፥ ልሩጥ አለው። ኢዮአብም፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም ወሬ የምትወስድ አይደለህምና ትሮጥ ዘንድ ለምን ትወድዳለህ? አለ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደ ገና ኢዮአብን፣ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፣ “ልጄ ሆይ፣ መሄድ ለምን አስፈለገህ? ሽልማት የሚያሰጥህ ምን የምሥራች ይዘህ ነው?” ብሎ መለሰለት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽም እንደገና ኢዮአብን፥ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፥ “ልጄ ሆይ፥ የምሥራቹ ሽልማት እንደማያሰጥህ እያየህ መሄድ ለምን አስፈለገህ?” ብሎ መለሰለት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ኢዮአብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከትዬ፥ እባክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮአብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮጣለህ? ተመለስ፤ ብትሄድ ይች ወሬ ለጥቅም አትሆንህምና” አለ። 参见章节 |