Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ግን፦ እግዚአብሔር ጠላቶቹን እንደተበቀለለት ሮጬ ለንጉሥ የምሥራች ልንገር አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በዚህ ጊዜ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ፣ “እግዚአብሔር ጠላቶቹን የተበቀለለት መሆኑን ሮጬ ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ፥ “ጌታ ጠላቶቹን የተበቀለለት መሆኑን ሮጬ ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ኢዮአብን “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው የሚገልጠውን መልካም ወሬ ይዤ ወደ ንጉሡ ልሩጥ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:19
15 交叉引用  

ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፦ እነሆ አንተና ልጅህ አኪማአስ የአብያታርም ልጅ ዮናታን ሁለቱ ልጆቻችሁ በደኅና ወደ ከተማ ተመለሱ።


እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን ልጆቻቸው በዚያ ከእነርሱ ጋር አሉ፥ የምትሰሙትን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላኩልኝ።


ዮናታንና አኪማአስ ተገልጠው ወደ ከተማ ይገቡ ዘንድ አልቻሉም ነበርና በዓይንሮጌል ተቀምጠው ነበር፥ አንዲትም ባሪያ ሄዳ ትነግራቸው ነበር፥ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ይነግሩት ነበር።


ኢዮአብም፦ በሌላ ቀን እንጂ ዛሬ ወሬ አትናገርም፥ የንጉሥ ልጅ ሞቶአልና ዛሬ ወሬ አትናገርም አለው።


እርሱም፦ እኔ ብሮጥ ምን ይገድዳል? አለ። እርሱም፦ ሩጥ አለው። አኪማአስም በሜዳው መንገድ በኩል ሮጠ፥ ኵሲንም ቀደመው።


እነሆም፥ ኵሲ መጣ፥ ኵሲም፦ እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቼአለሁ አለ።


ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካዎችዋም እንደ ተያዙ፥ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፥ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።


ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።


跟着我们:

广告


广告