Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዳዊትም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቈጠረ፥ ሻለቆችንና የመቶ አለቆችንም ሾመላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳዊት ዐብሮት የነበረውን ሕዝብ ቈጠረ፤ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዳዊት አብሮት የነበረውን ሕዝብ ቆጠረ፤ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ዳዊት ተከታዮቹን ሁሉ በአንድነት ከሰበሰበ በኋላ በሺህና በመቶ መድቦ ለእያንዳንዱ ቡድን የጦር መኰንን ሾመ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ቈጠረ፤ የሻ​ለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም በላ​ያ​ቸው ሾመ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:1
8 交叉引用  

ሙሴም ኢያሱን፦ ጕልማሶችን ምረጥልን፥ ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው።


አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው።


ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ አዋቂዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶም አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የአሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።


ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።


አለቆቹም ለሕዝቡ ነግረው በጨረሱ ጊዜ በየጭፍራው በሕዝቡ ላይ የጦር አለቆችን ይሹሙ።


ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ ሕዝቡንም አሰለፈ፥ እርሱም የእስራኤልም ሽማግሌዎች ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።


ሳኦልም በአጠገቡ የቆሙትን ባሪያዎቹን፦ ብንያማውያን ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ፥ በውኑ የእሴይ ልጅ እርሻና የወይን ቦታ ለሁላችሁ ይሰጣችኋልን? ሁላችሁንስ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋችኋልን?


ለራሱም የሻለቆችና የመቶ አለቆች ያደርጋቸዋል፥ እርሻውንም የሚያርሱ እህሉንም የሚያጭዱ የጦር መሣሪያውንና የሰረገሎቹንም ዕቃ የሚሠሩ ይሆናሉ።


跟着我们:

广告


广告