Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 17:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አሁን እንግዲህ ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እንዳይዋጡ፥ ፈጥናችሁ፦ ሳትዘገይ ተሻገር እንጂ በዚህች ሌሊት በምድረ በዳ መሻገሪያ አትደር ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አሁንም በፍጥነት ላኩና፣ ‘በምድረ በዳው ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፤ ሳትዘገይ ፈጥነህ መሻገር አለብህ፤ አለዚያ ግን ንጉሡና ዐብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አሁንም በፍጥነት ላኩና፥ ‘ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እንዳትዋጡ፥ በዚህች ሌሊት በምድረ በዳ መሻገሪያ እንዳታድር ሳትዘገይ ተሻገር፤’ ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት፤ አላቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም ጋር “እንግዲህ ዛሬ ሌሊት በበረሓ ውስጥ በሚገኘው በወንዙ መሻገሪያ ላይ እንዳያድር በፍጥነት መልእክተኛ ልካችሁ ለዳዊት ንገሩት! ነገር ግን እርሱና ተከታዮቹ ተይዘው እንዳይገደሉ በፍጥነት የዮርዳኖስን ወንዝ ይሻገሩ!” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 አሁን እን​ግ​ዲህ ንጉ​ሡና ከእ​ርሱ ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ዋጡ፥ ሳት​ዘ​ገይ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገር እንጂ በዚ​ህች ሌሊት በም​ድረ በዳ ውስጥ በሜ​ዳው አት​ደር ብለው ለዳ​ዊት ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈጥ​ና​ችሁ ላኩ” አላ​ቸው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 17:16
14 交叉引用  

ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን ባሪያዎቹን ሁሉ፦ ተነሡ፥ እንሽሽ፥ ያለዚያ ከአቤሴሎም እጅ የሚድን ከእኛ የለምና፥ መጥቶም እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን ከተማይቱንም በሰይፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ አላቸው።


እኔም፥ እነሆ፥ ከእናንተ ዘንድ ወሬ እስኪመጣልኝ ድረስ በምድረ በዳው መሻገርያ እቆያለሁ አለው።


ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያ ከአንተ ጋር አይደሉምን? ከንጉሡ ቤትም የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው።


ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።


በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን።


ዮናታንም ደግሞ፦ ቶሎ ፍጠን፥ አትቆይ ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ፥ የዮናታንም ብላቴና ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ።


跟着我们:

广告


广告