Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የጽሩያም ልጅ አቢሳ ንጉሡን፦ ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን ስለምን ይረግማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፣ “ይህ የሞተ ውሻ፣ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሻገርና ራሱን ልቍረጠው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፤ “ይህ የሞተ ውሻ፥ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚህ ጊዜ የጸሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! ይህ የሞተ ውሻ ጌታዬን ንጉሡን እንዴት ይራገማል? እኔ ሄጄ ራሱን ልቊረጠው!” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢ​ሳም ንጉ​ሡን አለው፥ “ይህ የሞተ ውሻ ጌታ​ዬን ንጉ​ሡን ስለ​ምን ይረ​ግ​ማል? ልሻ​ገ​ርና ራሱን ልቍ​ረ​ጠው፤”

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 16:9
13 交叉引用  

የጽሩያ ልጅ አቢሳ ግን፦ ሳሚ እግዚአብሔር የቀባውን ሰድቦአልና ሞት የተገባው አይደለምን? አለ።


ዳዊትም፦ እናንተ የጽሩያ ልጆች፥ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ ስለ ምን ጠላቶች ትሆኑብኛላችሁ? ዛሬስ በእስራኤል ዘንድ ሰው ሊሞት ይገባልን? ዛሬስ በእስራኤል ላይ እንደ ነገሥሁ አላወቅሁምን? አለ።


ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ገደሉት።


አበኔርም በኢያቡስቴ ቃል እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፥ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኃጢአት ትከስሰኛለህ፥ በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን?


እርሱም፦ የሞተ ውሻ ወደምመስል ወደ እኔ የተመለከትህ እኔ ባሪያህ ምንድር ነኝ? ብሎ እጅ ነሣ።


ፈራጆችን አትስደብ፥ የሕዝብንም አለቃ አትርገመው።


ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ አይተው፦ ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? አሉት።


ጳውሎስም፦ ወንድሞች ሆይ፥ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው፤ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር ተብሎ ተጽፎአልና አላቸው።


ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።


የእስራኤል ንጉሥ ማንም ለማሳደድ መጥቶአል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን ታሳድዳለህን?


跟着我们:

广告


广告