Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 16:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የዳዊትም ወዳጅ አርካዊው ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ፦ ሺህ ዓመት ያንግሥህ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ኩሲም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ሑሻይም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዳዊት ታማኝ ወዳጅ ሑሻይ አቤሴሎምን ባገኘው ጊዜ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ይሁን!” እያለ ጮኸ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ አቤ​ሴ​ሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ንጉሥ ሆይ! ሽህ ዓመት ያን​ግ​ሥህ” አለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 16:16
13 交叉引用  

ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ በመጣ ጊዜ፥ አርካዊው ኩሲ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።


ወደ ከተማ ግን ተመልሰህ ለአቤሴሎም፦ ንጉሥ ሆይ፥ ባሪያ እሆንሃለሁ፥ አስቀድሞ ለአባትህ ባሪያ እንደ ነበርሁ እንዲሁ አሁን ለአንተ ባሪያ እሆንሃለሁ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር ከንቱ ታደርግለኛለህ።


የዳዊትም ወዳጅ ኩሲ ወደ ከተማ መጣ፥ አቤሴሎምም ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊትንም አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ ይላሉ።


በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቅቡት፤ ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ ‘ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ በሉ።


የናታንም ልጅ ዓዛርያስ የሹሞች አለቃ ነበረ፤ የናታንም ልጅ ዛቡድ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ ነበረ፤


የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብተውም ንጉሥ አደረጉትና “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ እጃቸውን አጨበጨቡ።


ከለዳውያኑም ንጉሡን በሶርያ ቋንቋ፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፥ ለባሪያዎችህ ሕልምህን ንገር፥ እኛም ፍቺውን እናሳይሃለን ብለው ተናገሩት።


ንግሥቲቱም ስለ ንጉሡና ስለ መኳንንቱ ቃል ወደ ግብዣ ቤት ገባች፥ ንግሥቲቱም ተናገረች እንዲህም አለች፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ፥ አሳብህ አያስቸግርህ፥ ፊትህም አይለወጥ።


ዳንኤልም ንጉሡን፦ ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።


የዚያን ጊዜም አለቆቹና መሳፍንቱ ወደ ንጉሡ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።


ሳሙኤልም ለሕዝቡ ሁሉ፦ ከሕዝቡ ሁሉ እርሱን የሚመስል እንደሌለ እግዚአብሔር የመረጠውን ታያላችሁን? አላቸው፥ ሕዝቡም ሁሉ፦ ንጉሥ ሕያው ይሁን እያሉ እልልታ አደረጉ።


跟着我们:

广告


广告