Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 16:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዳዊትም ከተራራው ራስ ጥቂት ፈቀቅ ባለ ጊዜ የሜምፊቦስቴ ባሪያ ሲባ ሁለት መቶ እንጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም በለስ፥ አንድ አቁማዳም ወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ተገናኘው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት ዕልፍ ብሎ እንደ ሄደ፣ ሲባ የተባለው የሜምፊቦስቴ አገልጋይ፣ ሁለት መቶ እንጀራ፣ አንድ መቶ ጥፍጥፍ ዘቢብ፣ አንድ መቶ ጥፍጥፍ በለስና አንድ አቍማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ሊገናኘው መጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደ ሄደ፥ ጺባ የተባለው የመፊቦሼት አገልጋይ፥ ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ ጥፍጥፍ ዘቢብ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ሊያገኘው መጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዳዊት ከኮረብታው ጫፍ ባሻገር ገና ጥቂት እንደ ሄደ ጺባ ተብሎ የሚጠራው የመፊቦሼት አገልጋይ በድንገት አገኘው፤ እርሱም ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ የዘቢብ ጥፍጥፍ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና በወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይነዳ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዳዊ​ትም ከተ​ራ​ራው ራስ ጥቂት እልፍ አለ። እነ​ሆም፥ የሜ​ም​ፌ​ቡ​ስቴ አገ​ል​ጋይ ሲባ ሁለት መቶ እን​ጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም ተምር፥ አንድ አቁ​ማ​ዳም ወይን ጠጅ የተ​ጫኑ ሁለት አህ​ዮች እየ​ነዳ ተገ​ና​ኘው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 16:1
17 交叉引用  

ዳዊትም ተከናንቦ ያለ ጫማ እያለቀሰ ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው እያለቀሱ ወጡ።


ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ በመጣ ጊዜ፥ አርካዊው ኩሲ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።


ከእርሱም ጋር ብንያማውያን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፥ የሳኦልም ቤት ባሪያ ሲባ ከእርሱም ጋር አሥራ አምስቱ ልጆችና ሀያው ባሪያዎች ነበሩ፥ በንጉሡም ፊት ፈጥነው ዮርዳኖስን ተሻገሩ።


ቤርዜሊም እጅግ ያረጀ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነበረ፥ እጅግም ትልቅ ሰው ነበረና ንጉሡ በመሃናይም ሳለ ይቀልበው ነበር።


ደግሞም በእስራኤል ዘንድ ደስታ ሆኖአልና እስከ ይሳኮርና እስከ ዛብሎን እስከ ንፍታሌምም ድረስ ለእርሱ አቅራቢያ የነበሩ በአህያና በግመል በበቅሎና በበሬ ላይ እንጀራና ዱቄት የበለስ ጥፍጥፍና የዘቢብ ዘለላ የወይንም ጠጅ ዘይትም በሬዎችንና በጎችንም በብዙ አድርገው ያመጡ ነበር።


እኔም፥ እነሆ፥ ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በምጽጳ እኖራለሁ፥ እናንተ ግን ወይንንና የበጋ ፍሬ ዘይትንም አከማቹ፥ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፥ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።


አይሁድ ሁሉ ከተሰደዱበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ፥ ወደ ይሁዳም አገር ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ መጡ፥ ወይንና የበጋንም ፍሬ እጅግ ብዙ አከማቹ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነበረ።


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


ከዚያም ደግሞ ወደ ፊት ትሄዳለህ፥ ወደ ታቦር ወደ ትልቁ ዛፍ ትደርሳለህ፥ በዚያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍየል ጠቦቶች፥ ሁለተኛው ሦስት ዳቦ፥ ሦስተኛውም የወይን ጠጅ አቁማዳ ይዘው ወደ እግዚአብሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ያገኙሃል፥


እሴይም እንጀራና የወይን ጠጅ አቁማዳ የተጫነ አህያ የፍየልም ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።


አቢግያም ፈጥና ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት አቁማዳ የወይን ጠጅ፥ አምስትም የተዘጋጁ በጎች፥ አምስትም መስፈሪያ ጥብስ እሸት፥ አንድ መቶ ዘለላ ዘቢብ፥ ሁለት መቶም የበለስ ጥፍጥፍ ወሰደች፥ በአህዮችም ላይ አስጫነች።


跟着我们:

广告


广告