Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ንጉሡም ሳዶቅን፦ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፥ በእግዚአብሔር ዓይን ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እርሱንና ማደሪያውን ያሳየኛል፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማዪቱ ይዘህ ተመለስ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ እርሱ እኔንም መልሶ ታቦቱንና ማደሪያውን እንደ ገና ለማየት ያበቃኛል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከዚያም ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ከተማይቱ ይዘህ ተመለስ፤ በጌታ ፊት ሞገስ ያገኝሁ እንደሆነ፥ እርሱ እኔንም መልሶ ታቦቱንና ማደሪያውን ያሳየኛል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ከተማይቱ መልሰህ ውሰድ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ያገኘሁ እንደ ሆነ አንድ ቀን ታቦቱንና ማደሪያውን እንዳይ ይፈቅድልኝ ይሆናል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ንጉ​ሡም ሳዶ​ቅን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ ከተማ መልስ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሞገስ አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ፥ መልሶ እር​ሷ​ንና ክብ​ሯን ያሳ​የ​ኛል፤

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 15:25
19 交叉引用  

የእግዚአብሔርንም ታቦት አገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ በስፍራው አኖሩት፥ ዳዊትም የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።


ንጉሡ ነቢዩን ናታንን፦ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፥ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በመጋረጆች ውስጥ እንደ ተቀመጠ እይ አለው።


በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።


ሙሴም እግዚአብሔርን፦ እነሆ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ከእኔም ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም፦ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ።


አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው።


ሕዝቅያስም፦ ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው? ብሎ ነበር።


ስለዚህ ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፥ በበረቱ ላይ እጅግ ይጮኻል፥ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።


የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ።


跟着我们:

广告


广告