Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ባሪያህ ኢዮአብ የዚህ ነገር መልክ እንዲለውጥ አደረገ፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ጠቢብ እንደ ሆነ፥ አንተም ጌታዬ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ታውቅ ዘንድ ጠቢብ ነህ አለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ የመሰለ ጥበብ ስላለው፣ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም የነገሩን መልክ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ ያለው ጥበብ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ ስለሚመስል፥ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እርሱም ይህን ያደረገው ነገሮችን ሁሉ ለማስተካከል በማሰብ ነው፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበበኛ ነህ፤ የሚሆነውንም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይህን ነገር እና​ገር ዘንድ እን​ድ​መጣ ይህን ምክር ያደ​ረገ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መል​አከ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ጥበ​በኛ ነህ፤”

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 14:20
12 交叉引用  

ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።


እኔም ባሪያህ፦ መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል ያጽናናኛል፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን አልሁ።


እኔ ቅሉ በነፍሱ ላይ ብወነጅል ኖሮ ይህ ከንጉሥ ባልተሰወረም፥ አንተም በተነሣህብኝ ነበር አለው።


እርሱም እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፥ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፥ ደስም ያሰኘህን አድርግ።


የአባቴ ቤት ሁሉ በጌታዬ በንጉሡ ዘንድ ሞት የሚገባቸው ነበሩ፥ አንተ ግን እኔን ባሪያህን በገበታህ በሚበሉ መካከል አስቀመጥኸኝ፥ ለንጉሥ ደግሞ ለመናገር ምን መብት አለኝ?


ዳዊትም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ በኋላቸው ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ አትውጣ።


አንኩስም መልሶ ዳዊትን፦ እንደ አምላክ መልእክተኛ በዓይኔ ፊት መልካም እንደ ሆንህ አውቃለሁ፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች፦ ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም አሉ።


跟着我们:

广告


广告