Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እርስዋም፦ ደም ተበቃዮችም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይጠፉ ልጄንም እንዳይገድሉ፥ ንጉሡ አምላኩን እግዚአብሔርን ያስብ አለች። እርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ከልጅሽ አንድ ጠጕር በምድር ላይ አይወድቅም አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እርሷም፣ “ደም ተበቃዮቹ ልጄን በማጥፋት የባሰ ጕዳት እንዳያደርሱ፣ ንጉሡ አምላኩን እግዚአብሔርን ይለምን” አለች። ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን! ከልጅሽ ራስ ላይ አንዲት ጠጕር እንኳ አትነካም” አላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! የልጄን ሞት ለመበቀል ኀላፊነት የተቀበለው ዘመዴ ሌላውን ልጄን በመግደል የባሰ ወንጀል እንዳይፈጽም ታደርገው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ” አለችው። ንጉሥ ዳዊትም “በልጅሽ ላይ ጒዳት መድረስ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ እንኳ አንዲቱ መሬት ላይ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሻለሁ” አላት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ያችም ሴት፥ “ለመ​ግ​ደል ባለ ደሞች እን​ዳ​ይ​በዙ፤ ልጄ​ንም እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉ​ብኝ ንጉሥ ፈጣ​ሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስብ” አለች። እር​ሱም፥ “የል​ጅ​ሽስ አን​ዲት የራሱ ጠጕር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ት​ወ​ድቅ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” አላት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 14:11
18 交叉引用  

አብራምም የስዶምን ንጉሥ አለው፤ ሰማይንና ምድርን ወደ ሚግዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፤


ልጆቼን ብትበድላቸው ከእኛ ጋር ያለ ሰው የለም እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ነው።


ንጉሡም፦ የሚናገርሽን አምጪልኝ፥ ከዚያም በኋላ ደግሞ አይነካሽም አለ።


ሴቲቱም፦ እኔ ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሥ አንድ ቃል ልናገር አለች፥ እርሱም፦ ተናገሪ አለ።


ንጉሡም ኢዮአብን፦ እነሆ፥ ይህን ነገር አድርጌአለሁ፥ እንግዲህ ሂድና ብላቴናውን አቤሴሎምን መልሰው አለው።


ሰሎሞንም “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደ ሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጕር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፤ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደ ሆነ ይሞታል፤” አለ።


ሕያው እግዚአብሔርን! ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ በእርሱም ይመካሉ።


ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደል፤ ባገኛው ጊዜ ይግደለው።


ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።


ደም ተበቃዩም ከመማፀኛው ከተማ ዳርቻ ውጭ ቢያገኘው፥ ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ቢገድለው፥ የደም ዕዳ አይሆንበትም፤


የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቍኦጥሮአል።


ሰለዚህ ምግብ ትበሉ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ይህ ለደኅንነታችሁ ይሆናልና፤ ከእናንተ ከአንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አትጠፋምና።”


ሕዝቡም ሳኦልን፦ በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኃኒት ያደረገ ዮናታን ይሞታልን? ይህ አይሁን፥ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጉር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም አሉት። ሕዝቡም እንዳይሞት ዮናታንን አዳነው።


ዮናታንም ዳዊትን፦ በደኅና ሂድ፥ እነሆ፥ እኛ ሁለታችን በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም እግዚአብሔር ይሁን ብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናል አለው። ዳዊትም ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ገባ።


ሳኦልም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ነገር ቅጣት አያገኝሽም ብሎ በእግዚአብሔር ማለላት።


跟着我们:

广告


广告