2 ሳሙኤል 13:34 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 አቤሴሎምም ኮበለለ። ጕበኛውም ጕልማሳ ዓይኑን ከፍ አደረገ፥ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም34 አቤሴሎምም ፈጥኖ ሸሸ። ለዘብ ጥበቃ የቆመውም ሰው ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ከርሱ በስተ ምዕራብ ካለው መንገድ ብዙ ሰዎች በተራራው ጥግ ቍልቍል ሲወርዱ አየ፤ ዘብ ጠባቂውም ሄዶ ለንጉሡ፣ “ከበስተ ሖሮናይም አቅጣጫ በኰረብታው ጥግ ላይ ሰዎች ቍልቍል ሲወርዱ አያለሁ” ብሎ ነገረው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 አቤሴሎምም ፈጥኖ ሸሸ። ለዘብ ጥበቃ የቆመውም ሰው ቀና ብሎ ተመለከተ፤ እነሆም፥ በኋላው ብዙ ሰዎች በተራራው ጥግ ሲመጡ አየ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 በዚህም ጊዜ አቤሴሎም ሸሽቶ አምልጦ ነበር፤ ለዘብ ጥበቃ ተረኛ የነበረውም ወታደር ልክ በዚያን ሰዓት ከሖርናይም ወደዚህ በሚመጣው መንገድ ላይ ካለው ኮረብታ ብዙ ሕዝብ ወደ ታች ሲወርድ አየ፤ ወደ ንጉሡም ቀርቦ ያየውን ሁሉ ተናገረ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።” 参见章节 |