Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 13:31 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ንጉሡም ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፥ በምድር ላይም ወደቀ፥ ባሪያዎቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀድደው በአጠገቡ ቆሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ንጉሡም ተነሥቶ ቆመ፤ ልብሱን ቀደደ፤ በመሬትም ላይ ተዘረረ፤ በአጠገቡ ቆመው የነበሩት አገልጋዮቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፤ በመሬትም ላይ ተዘረረ፤ በአጠገቡ ቆመው የነበሩት አገልጋዮቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀደዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ንጉሡ ከተቀመጠበት በመነሣት በሐዘን ልብሱን ቀዶ በመሬት ላይ ተዘረረ፤ በዚያ ከእርሱ ጋር የነበሩ አገልጋዮቹም በሐዘን ልብሳቸውን ቀደው በአጠገቡ በአክብሮት ቆሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን ቀደደ፤ በም​ድር ላይም ወደቀ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቁመው የነ​በሩ ብላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀደዱ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 13:31
8 交叉引用  

ሮቤልም ወደ ጕድጓድ ተመለሰ፥ እነሆም ዮሴፍ በጕድጓድ የለም ልብሱንም ቀደደ።


ያዕቆብም ልብሱን ቀደደ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ።


ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው ቀደዱ።


ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፥ ዳዊትም ጾመ፥ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ።


ገናም በመንገድ ሲሄዱ ለዳዊት፦ አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ገድሎአል፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም የሚል ወሬ መጣለት።


ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፦ ልብሳችሁን ቅደዱ፥ ማቅም ልበሱ፥ በአበኔርም ፊት አልቅሱ አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።


ኢዮብም ተነሣ መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፥


ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ፥ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።


跟着我们:

广告


广告