Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነሰነሰች፤ ጌጠኛ ልብሷን ቀደደች፤ ከዚያም እጇን በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ትዕማርም በራሷ ላይ ዐመድ ነስንሳ፤ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳደደች፤ እጇንም በራሷ ላይ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ትዕ​ማ​ርም አመድ ወስዳ በራ​ስዋ ላይ ነሰ​ነ​ሰች፤ በላ​ይዋ የነ​በ​ረ​ው​ንም ብዙ ኅብር ያለ​ውን ልብ​ስ​ዋን ቀደ​ደ​ችው፤ እጅ​ዋ​ንም በራ​ስዋ ላይ ጭና እየ​ጮ​ኸች ሄደች።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 13:19
10 交叉引用  

ሮቤልም ወደ ጕድጓድ ተመለሰ፥ እነሆም ዮሴፍ በጕድጓድ የለም ልብሱንም ቀደደ።


ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው ቀደዱ።


በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሳኦል ሰፈር አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፥ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ።


ወንድምዋም አቤሴሎም፦ ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበረን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፥ ወንድምሽ ነው፥ ይህን ነገር በልብሽ አትያዢው አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት ብቻዋን ተቀመጠች።


መርዶክዮስም የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ አመድም ነሰነሰ፥ ወደ ከተማይቱም መካከል ወጣ፥ ታላቅም የመረረ ጩኸት ጮኸ።


ከሩቅም ሆነው ዓይናቸውን ባነሡ ጊዜ አላወቁትም፥ ድምፃቸውንም አሰምተው አለቀሱ፥ እያንዳንዳቸውም መጐናጸፊያቸውን ቀደዱ፥ ወደ ላይም ወደ ራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ።


ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፥ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።


እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።


ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግምባራቸው ተደፉ፥ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።


በዚያም ቀን አንድ የብንያም ሰው ከሰልፍ እየበረረ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ወደ ሴሎ መጣ።


跟着我们:

广告


广告