Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 13:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እርስዋ መልሳ፦ ወንድሜ ሆይ፥ አይሆንም፥ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና አታሳፍረኝ፥ ይህንም ነውረኛ ሥራ አታድርግ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሷም እንዲህ አለችው፤ “እባክህ ወንድሜ ተው አይሆንም! አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አታድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርስዋም “አይሆንም ወንድሜ ሆይ! እባክህ አታዋርደኝ! የዚህ ዐይነቱ አሳፋሪ ተግባር በእስራኤል ተፈጽሞ አያውቅም! ስለዚህ ይህን ትልቅ ብልግና አትፈጽም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ አታ​ዋ​ር​ደኝ፤ እን​ዲህ ያለ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አይ​ገ​ባ​ምና ይህን ነው​ረኛ ሥራ አታ​ድ​ርግ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 13:12
12 交叉引用  

የአገሩ አለቃ የኤዊያዊ ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት ወሰዳርም ከእርስዋም ጋር ተኛ አስነወራትም።


የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከምድረ በዳ መጡ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ስንፍናን ስላደረገ አዘኑ እጅግም ተቈጡ እንዲህ አይደረግምን።


በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና።


ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ።


የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።


ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኃጢአቱን ይሸከማል።


ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።


ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።


ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፥ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ።


እኔም ቁባቴን ይዤ ቈራረጥኋት፥ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ኃጢአትና ስንፍና ስለ ተሠራ ወደ እስራኤል ርስት አገር ሁሉ ሰደድሁ።


跟着我们:

广告


广告