Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 13:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፥ ስምዋም ትዕማር ነበረ፥ የዳዊት ልጅ አምኖን ወደዳት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቈንጆ እኅት ነበረችው፤ እርሷንም የዳዊት ልጅ አምኖን ወደዳት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ትዕማር የምትባል ቆንጆ እኅት ነበረችው፤ የዳዊት ልጅ አምኖንም ወደዳት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የዳዊት ልጅ አቤሴሎም ውብ የሆነች ትዕማር ተብላ የምትጠራ፥ ገና ባል ያላገባች እኅት ነበረችው፤ አምኖን ተብሎ የሚጠራው ከዳዊት ልጆች አንዱ ትዕማርን ወደዳት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ለዳ​ዊት ልጅ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም አን​ዲት የተ​ዋ​በች እኅት ነበ​ረ​ችው፤ ስም​ዋም ትዕ​ማር ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጅ አም​ኖን ወደ​ዳት።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 13:1
15 交叉引用  

ያዕቆብም ራሔልን ወደደ እንዲህም አለ፦ ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባር ዓመት እገዛልሃለሁ።


ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።


ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ ብላቴናይቱንም ወደዳት ልብዋንም ደስ በሚያስኛት ነገር ተናገራት።


የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ።


እንዲህም ሆነ፥ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከምንጣፉ ተነሣ፥ በንጉሥም ቤት በሰገነት ላይ ተመላለሰ፥ በሰገነቱ ሳለ አንዲት ሴት ስትታጠብ አየ፥ ሴቲቱም መልከ መልካም ነበረች።


ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፥ አስቀድሞም ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፦ ተነሥተሽ ሂጂ አላት።


አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ ታመመ፥ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር።


ለአቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት፥ የሴቲቱም ልጅ ስም ትዕማር ነበረ፥ እርስዋም የተዋበች ሴት ነበረች።


ንጉሡም ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ፥ በሞዓባውያንና በአሞናውያን በኤዶማውያንም በሲዶናውያንና በሒታውያን ሴቶች፥ በብዙ እንግዶች ሴቶች ፍቅር ተነደፈ።


ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥


እነዚህ ሁሉ ከቁባቶች ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች።


跟着我们:

广告


广告