Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዳዊትም ኦርዮን፦ ወደ ቤትህ ሂድ፥ እግርህንም ታጠብ አለው። ኦርዮም ከንጉሡ ቤት ሲወጣ ማለፊያ የንጉሥ መብል ተከትሎት ሄደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም ዳዊት ኦርዮን፣ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም ማለፊያ ምግብ አስከትሎ ላከለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚያም ዳዊት ኦርዮንን፥ “በል እንግዲህ ወደ ቤትህ ወርደህ እግርህን ታጠብ” አለው። ኦርዮን ከቤተ መንግሥት ተሰናብቶ ወጣ፤ ንጉሡም የምግብ ስጦታ ላከለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህም በኋላ ዳዊት ኦርዮን “እንግዲህ ወደ ቤትህ ሂድና እግርህን ታጠብ” አለው፤ ኦርዮም ከዳዊት ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ዳዊትም ወዲያውኑ የምግብ ስጦታ ላከለት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ወደ ቤትህ ሂድ፤ እግ​ር​ህ​ንም ታጠብ” አለው። ኦር​ዮም ከን​ጉሡ ቤት ሲወጣ አንድ የን​ጉሥ መል​እ​ክ​ተኛ ተከ​ተ​ለው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 11:8
11 交叉引用  

ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፤


ጌቶቼ ሆይ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ ከዚያም እደሩ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁም ትሄዳላችሁ። እነርሱም፤ በአደባባዩ እናድራለን እንጂ አይሆንም አሉት።


ስምዖንም አወጣላቸው። ሰውዮውም እነዚያን ስዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው ውኃ አመጣላቸው እግራቸውንም ታጠቡ ለአህዮቻቸው አበቅ ስጣቸው።


በፊቱም ካለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው የብንያም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ እነርሱም ጠጡ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው።


ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው!


ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም።


ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች።


እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።


跟着我们:

广告


广告