Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በደብዳቤውም፦ ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፥ ተመትቶም ይሞት ዘንድ ከኋላው ሽሹ ብሎ ጻፈ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በደብዳቤውም ላይ፣ “ኦርዮ ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በደብዳቤውም ላይ፥ “ኦርዮን ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የጻፈውም ቃል “ኦርዮን ጦርነቱ በተፋፋመበት ግንባር አሰልፈው፤ ከዚያም አንተ ወደ ኋላ አፈግፍገህ እርሱ እንዲገደል አድርገው” የሚል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 11:15
12 交叉引用  

ኢዮአብም ከተማይቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው።


የከተማይቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ተዋጉ፥ ከዳዊትም ባሪያዎች ከሕዝቡ አንዳንዱ ወደቁ፥ ኬጢያዊው ኦርዮም ደግሞ ሞተ።


አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል፥ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።


ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።


በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይፈረድምና ስለዚህ በሰው ልጆች ውስጥ ልባቸው ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።


የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፥ ማንስ ያውቀዋል?


ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ፥ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።


ሳኦልም ዳዊትን፦ ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፥ እርስዋን እድርልሃለሁ፥ ብቻ ቀልጣፋ ልጅ ሁንልኝ፥ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል አለው። ሳኦልም፦ የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን ይል ነበር።


ሳኦልም፦ ወጥመድ ትሆነው ዘንድ፥ የፍልስጥኤማውያንም እጅ በእርሱ ላይ ትሆን ዘንድ እርስዋን እድርለታለሁ አለ፥ ሳኦልም ዳዊትን፦ ዛሬ ሁለተኛ አማች ትሆነኛለህ አለው።


ሳኦልም ዳዊትን በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ፦ የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ ከመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት አላቸው።


跟着我们:

广告


广告