Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 1:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፥ የሳኦል ጋሻ በዘይት እንዳልተቀባ፥ የኃያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፥ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ ጠል አያረስርሳችሁ፤ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቍርባን እህል የሚያበቅሉም ዕርሻዎች አይኑራቸው፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሷልና፤ የሳኦል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥ ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤ ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ። የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤ የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 1:21
14 交叉引用  

ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።


በነጋውም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።


አንገትሽ ለሰልፍ ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራው እንደ ዳዊት ግንብ ነው፥ ሺህ ጋሻ የኃያላንም መሣሪያ ሁሉ ተንጠልጥሎበታል።


ማዕዱን ያዘጋጃሉ፥ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፥ ይበሉማል፥ ይጠጡማል፥ እናንተ መሳፍንት ሆይ፥ ተነሡ፥ ጋሻውን አዘጋጁ።


ባድማ አደርገዋለሁ፥ አይቆረጥም፥ አይኮተኮትም፥ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፥ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት ፈሳሾቹንም ከለከልሁ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፥ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ።


የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዶአል፥ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።


የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?


የእግዚአብሔር መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ፥ እግዚአብሔርን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምና የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ አለ።


ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው፦ በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፥ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፥ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ።


ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፥ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።


በማግሥቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።


跟着我们:

广告


广告