Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 9:37 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 የኤልዛቤልም ሬሳ በኢይዝራኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆናልና ማንም “ይህች ኤልዛቤል ናት፤” ይል ዘንድ አይችልም፤’ ብሎ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ሥጋዋም በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ እንደ ፍግ ስለሚሆን፣ ማንም ሰው፣ ‘ይህች ኤልዛቤል ናት’ ሊል አይችልም ብሎ የተናገረው ቃል ይህ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርሷነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርስዋነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልም ሬሳ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆ​ና​ልና ማንም፦ ይህች ኤል​ዛ​ቤል ናት ይል ዘንድ አይ​ች​ልም ብሎ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 9:37
14 交叉引用  

ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነፍሱም መልካምን ባትጠግብ መቃብርንም ባያገኝ፥ እኔ ስለ እርሱ፦ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።


ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፥ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፥ ሬሳቸውም በአደባባይ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኗል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።


በክፉ ሞት ይሞታሉ፥ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ፥ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።


አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።


በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፥ አይለቀስላቸውም፥ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይከማቹም አይቀበሩምም።


ወደ ንጉሡም ወደ አደባባይ ገቡ፥ ክርታሱንም በጸሐፊው በኤሊሳማ ጓዳ አኑረውት ነበር፥ ቃሉንም ሁሉ በንጉሡ ጆሮ ተናገሩ።


በዚያን ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ።


በወደዱአቸውና ባመለኩአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፥ አያከማቹአቸውም አይቀብሩአቸውምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።


የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንምም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።


跟着我们:

广告


广告