Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 9:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሁሉም ፈጥነው ልባሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት፤ ቀንደ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል!” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያ ሁሉም ቶሎ ብለው ልብሳቸውን እያወለቁ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ ከዚያም መለከት ነፍተው፣ “ኢዩ ነግሧል” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በሰ​ሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥ​ነው ልብ​ሳ​ቸ​ውን ወሰዱ፤ በሰ​ገ​ነቱ መውጫ እር​ከን ላይም ከእ​ግሩ በታች አነ​ጠ​ፉት፥ መለ​ከ​ትም እየ​ነፉ፥ “ኢዩ ነግ​ሦ​አል” አሉ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 9:13
12 交叉引用  

አቤሴሎምም በእስራኤል ነገድ ሁሉ፦ የቀንደ መለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፦ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ በሉ የሚሉ ጉበኞች ላከ።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊትንም አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ ይላሉ።


በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ይቅቡት፤ ቀንደ መለከትም ነፍታችሁ ‘ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!’ በሉ።


ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፤ ቀንደ መለከትም ነፉ፤ ሕዝቡም ሁሉ “ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ!” አሉ።


የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብተውም ንጉሥ አደረጉትና “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ እጃቸውን አጨበጨቡ።


እነሆም፥ ንጉሡ እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር አለቆችና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የአገሩም ሕዝብ ሁል ደስ ብሎአቸው ቀንደ መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።


እነርሱም “ሐሰት ነው፤ ያለውን ንገረን፤” አሉት፤ እርሱም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤’ ብሎ እንዲህ እንዲህ ነገረኝ፤” አላቸው።


ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር።


跟着我们:

广告


广告