Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ኢዩም ወደ ጌታው አገልጋዮች ወጣ፤ እነርሱም “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን መጣብህ?” አሉት። እርሱም “ሰውዮውንና ንግግሩን ታውቃላችሁ፤” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ኢዩ ወጥቶ የጦር አለቆች ወደሆኑት ጓደኞቹ እንደ ደረሰ፣ ከመካከላቸው አንዱ “ሁሉም ነገር ሰላም ነው? ይህ እብድ ወደ አንተ የመጣው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ የሚናገረውን እናንተም ታውቃላችሁ” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ኢዩም፦ ጓደኞቹ ወደ ሆኑት ወደ ጦር መኰንኖቹ በመጣ ጊዜ “ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ከአንተ ምን ይፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ኢዩም፦ ጓደኞቹ ወደሆኑት ወደ ጦር መኰንኖቹ በመጣ ጊዜ “ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ከአንተ ምን ይፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ኢዩም ወደ ጌታው ብላ​ቴ​ኖች ወጣ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ፌዝ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 9:11
16 交叉引用  

ትቀበላትም ዘንድ ሩጥና ‘በደኅናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅሽስ ደኅና ነውን?’ በላት፤” አለው። እርስዋም “ደኅና ነው፤” አለች።


ግያዝም ንዕማንን ተከተለው፤ ንዕማንም ወደ እርሱ ሲሮጥ ባየው ጊዜ ሊገናኘው ከሠረገላው ወርዶ “ሁሉ ደኅና ነውን?” አለው።


እነርሱም “ሐሰት ነው፤ ያለውን ንገረን፤” አሉት፤ እርሱም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤’ ብሎ እንዲህ እንዲህ ነገረኝ፤” አላቸው።


በኢይዝራኤልም ግንብ ላይ የቆመው ሰላይ የኢዩ ጭፍራ ሲመጣ አይቶ “ጭፍራ አያለሁ፤” አለ። ኢዮራምም “የሚገናኘው ፈረሰኛ ላክ፤ እርሱም ‘ሰላም ነውን?’ ይበለው፤” አለ።


ሁለተኛም ፈረሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነርሱም ደርሶ “ንጉሡ እንዲህ ይላል ‘ሰላም ነውን?’” አለ። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ አልፈህ ተከተለኝ፤” አለ።


በዚያም በደረስህ ጊዜ የናሜሲን ልጅ የኢዮሣፍጥን ልጅ ኢዩን ታገኘዋለህ፤ ገብተህም ከወንድሞቹ መካከል አስነሣው፤ ወደ ጓዳም አግባው።


ኢዮራምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ! ሰላም ነውን?” አለ። እርሱም “የእናትህ የኤልዛቤል ግልሙትናዋና መተትዋ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።


እውነትም ታጥቶአል፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ፥ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ።


እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በእግር ግንድና በዛንጅር ታኖረው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።


የበቀል ወራት መጥቶአል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ያውቃል፥ ከኃጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሰንፎአል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።


ዘመዶቹም ሰምተው፦ አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።


ከእነርሱም ብዙዎች፦ “ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ?” አሉ።


ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም፦ ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው፦ አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል አሉ።


እንዲህም ብሎ ስለ ራሱ ሲመልስ ፊስጦስ በታላቅ ድምፅ፦ “ጳውሎስ ሆይ፥ አብድሃል እኮ፤ ብዙ ትምህርትህ ወደ እብደት ያዞርሃል” አለው።


እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃይለኞች ናችሁ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን።


እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።


跟着我们:

广告


广告