Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እርሱም የሞተውን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ሴት ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ወደ ንጉሥ ጮኸች፤ ግያዝም “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ኤልሳዕ ልጇን ከሞት ያስነሣላት ሴት ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ለማመልከት ወደ ንጉሡ ዘንድ የቀረበችውም፣ ኤልሳዕ የሞተውን ልጅ እንዴት እንዳስነሣ ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ወቅት ነበር። ግያዝም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣው ልጇም ይህ ነው” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጇ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጅዋ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እር​ሱም የሞ​ተ​ውን ሕፃን እንደ አስ​ነሣ ለን​ጉሡ ሲና​ገር፥ እነሆ፥ ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያ​ዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤል​ሳ​ዕም ያስ​ነ​ሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 8:5
16 交叉引用  

ለኢይዝራኤላዊውም ለናቡቴ በሰማርያ ንጉሥ በአክዓብ ቤት አጠገብ የወይን ቦታ ነበረው።


ሎሌውንም ግያዝን “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው።


ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዐይኖቹን ከፈተ።


ከባሪያዎቹም አንዱ “ጌታዬ ሆይ! እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል፤” አለ።


የእስራኤልም ንጉሥ በቅጥር ላይ በተመላለሰ ጊዜ አንዲት ሴት “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ፤” ብላ ወደ እርሱ ጮኸች።


ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቀ፤ ነገረችውም። ንጉሡም “የነበረላትን ሁሉ፥ መሬትዋንም ከተወች ጀምራ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የእርሻዋን ፍሬ ሁሉ መልስላት፤” ብሎ ስለ እርስዋ ጃንደረባውን አዘዘ።


ሚስቱም ዞሳራና ወዳጆቹ ሁሉ፦ ቁመቱ አምሳ ክንድ የሆነ ግንድ ይደረግ፥ ነገም መርዶክዮስ ይሰቀልበት ዘንድ ለንጉሡ ተናገር፥ ደስም ብሎህ ከንጉሡ ጋር ወደ ግብዣው ግባ አሉት። ነገራቸውም ሐማን ደስ አሰኘው፥ ግንዱንም አስደረገ።


እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


ሄደችም፤ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፤ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።


ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ አውቆ፦ ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ይህ ድምፅህ ነውን? አለው። ዳዊትም፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው አለው።


跟着我们:

广告


广告