Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 8:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰባቱም ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሴቲቱ ከፍልስጥኤም አገር ተመለሰች፤ ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ልትጮኽ ወደ ንጉሡ ወጣች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሰባት ዓመት በኋላም፣ ከፍልስጥኤም ምድር ተመልሳ መጣች፤ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ አቤቱታ ለማቅረብም ወደ ንጉሡ ሄደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰባ​ቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ተመ​ለ​ሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልት​ጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች።

参见章节 复制




2 ነገሥት 8:3
10 交叉引用  

እንዲሁም የቴቁሔይቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግምባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፥ እጅ ነሥታም፦ ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ አለች።


በጠራትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። እርሱም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ አሳብ አሰብሽልኝ፤ አሁንስ ምን ላድርግልሽ? ለንጉሥ ወይስ ለሠራዊት አለቃ ልንገርልሽን? በላት፤” አለው፤ እርስዋም “እኔ በወገኔ መካከል ተቀምጫለሁ፤” ብላ መለሰች።


የእስራኤልም ንጉሥ በቅጥር ላይ በተመላለሰ ጊዜ አንዲት ሴት “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እርዳኝ፤” ብላ ወደ እርሱ ጮኸች።


ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተሰብዋም ጋር ሄዳ በፍልስጥኤም አገር ሰባት ዓመት ተቀመጠች።


ንጉሡም ከእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ከግያዝ ጋር “ኤልሳዕ ያደረገውን ተአምራት ሁሉ ንገረኝ፤” እያለ ይጫወት ነበር።


ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቀ፤ ነገረችውም። ንጉሡም “የነበረላትን ሁሉ፥ መሬትዋንም ከተወች ጀምራ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የእርሻዋን ፍሬ ሁሉ መልስላት፤” ብሎ ስለ እርስዋ ጃንደረባውን አዘዘ።


የድሀውንና የችግረኛውን ፍርድ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።


እርስዋም ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከተቀመጠችበት ስፍራ ወጣች፤ ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ በመንገድ ሄዱ።


跟着我们:

广告


广告