Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 8:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከአክዓብም ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገልዓድ ሊጋጠም ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 አካዝያስም ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋራ ሆኖ በሶርያ ንጉሥ በአዛሄል ላይ ለመዝመት ወደ ራሞት ገለዓድ ሄደ፤ ሶርያውያንም በዚያ ኢዮራምን አቈሰሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በሶርያው ንጉሥ አዛሄል ላይ በታወጀው ጦርነት፥ ንጉሥ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ተባባሪ በመሆን ዘመተ፤ የሁለቱም ነገሥታት ሠራዊት ከሶርያውያን ሠራዊት ጋር በገለዓድ በምትገኘው በራሞት ጦርነት በገጠመ ጊዜ ኢዮራም በውጊያው ላይ ቆሰለ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በሶርያው ንጉሥ አዛሄል ላይ በታወጀው ጦርነት፥ ንጉሥ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ተባባሪ በመሆን ዘመተ፤ የሁለቱም ነገሥታት ሠራዊት ከሶርያውያን ሠራዊት ጋር በገለዓድ በምትገኘው በራሞት ጦርነት በገጠመ ጊዜ ኢዮራም በውጊያው ላይ ቈሰለ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊጋ​ጠም ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 8:28
18 交叉引用  

ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ፥ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።


የእስራኤልም ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ወጡ።


በሬማት ዘገለዓድ የጌበር ልጅ ነበረ፤ ለእርሱም በገለዓድ ያሉት የምናሴ ልጅ የኢያዕር መንደሮች ነበሩ፤ ለእርሱም ደግሞ በባሳን በአርጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥርና የናስ መወርወሪያዎች የነበረባቸው ስድሳ ታላላቅ ከተሞች ነበሩበት፤


ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥ “የሞዓብ ንጉሥ ዐምዖብኛልና ከእኔ ጋር በሞዓብ ላይ ለሰልፍ ትሄዳለህን?” ብሎ ላከ። እርሱም “እወጣለሁ፤ እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ፥ ፈረሶቼም እንደ ፈረሶችህ ናቸው፤” አለ።


በነጋውም የአልጋ ልብስ ወስዶ በውሃ ነከረው በፊቱም ላይ ሸፈነው፤ ሞተም። አዛሄልም በፋንታው ነገሠ።


ንጉሡም ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን በሬማት ያቈሰሉትን ቈስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። የአክዓብም ልጅ ኢዮራም ታምሞ ነበርና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።


ነቢዩም ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው “ወገብህን ታጥቀህ ይህን የዘይት ማሰሮ በእጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገለዓድም ሂድ።


እንዲሁም የናሜሲ ልጅ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ ተማማለ። ኢዮራምና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል የተነሣ ሬማት ዘገለዓድን ይጠብቁ ነበር።


ንጉሡ ኢዮራም ግን ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር በተዋጋ ጊዜ ሶርያውያን ያቈሰሉትን ቍስል ይታከም ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመልሶ ነበር። ኢዩም “ልባችሁስ ከእኔ ጋር ከሆነ በኢይዝራኤል እንዳያወራ ማንም ከከተማ ኮብልሎ አይውጣ፤” አለ።


ኢዮራምም በዚያ ታምሞ ተኝቶ ነበርና ኢዩ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ። የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ኢዮራምን ለማየት ወርዶ ነበር።


የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋጠሙትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ረዳው፤ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።


ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ ሆኖብሃል።


በምክራቸውም ሄደ፤ ከእስራኤልም ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለአድ ሊዋጋ ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራንም አቈሰሉት።


በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።


ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥


跟着我们:

广告


广告