Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 8:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኤልሳዕም “ሂድ፤ ‘መዳንስ ትድናለህ፤’ በለው፤ ነገር ግን እንዲሞት እግዚአብሔር አሳይቶኛል፤” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኤልሳዕም፣ “ሂድና፣ ‘መዳኑንስ በርግጥ ትድናለህ’ በለው፤ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጾልኛል” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኤልሳዕም “ቤንሀዳድ እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤ አንተ ግን ትድናለህ ብለህ ንገረው” አለው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ መዳ​ንስ ትድ​ና​ለህ በለው፤ ነገር ግን እን​ዲ​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 8:10
16 交叉引用  

ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።


ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እንደ አንተ ያለ ብልህ አዋቂም ሰው የለም እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና።


ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ “ሚክያስ ሆይ! ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ እንሂድን? ወይስ እንቅር?” አለው፤ እርሱም “ውጣና ተከናወን፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታል፤” ብሎ መለሰለት።


ኤልያስም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ልከሃልና ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም’” አለው።


ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤” በላቸው’” አለው። ኤልያስም ሄደ።


ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል ግን፥ እግዚአብሔር ያሳየኝ ቃል ይህ ነው።


እግዚአብሔርም ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞች ተናገርሁ።


በአራጣ ቢያበድር፥ ትርፎቻም ቢወስድ፥ በውኑ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፥ ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል፥ ደሙ በላዩ ላይ ይሆናል።


በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፥ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ፥ እርስዋም ታላቁን ቀላይና ምድርን በላች።


እንዲህም አሳየኝ፥ እነሆም፥ ጌታ ቱንቢውን ይዞ በቱንቢ በተሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነበረ።


እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።


በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።


跟着我们:

广告


广告