Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከዚያም ወዲያ እርስ በርሳቸው “መልካም አላደረግንም፤ ዛሬ የመልካም ምስራች ቀን ነው፤ እኛም ዝም ብለናል፤ እስኪነጋም ድረስ ብንቆይ በደለኞች እንሆናለን፤ ኑ፤ እንሂድ፤ ለንጉሥ ቤተሰብ እንናገር፤” ተባባሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርስ በርሳቸውም፣ “ያደረግነው ትክክል አይደለም፤ ዕለቱ የምሥራች ቀን ነው፤ እኛ ግን የራሳችን ብቻ አደረግነው፤ እስኪነጋም ከቈየን በደለኞች እንሆናለን፤ ስለዚህ ወደ ቤተ መንግሥት በፍጥነት ሄደን እንንገር” ተባባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚህም በኋላ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “መልካም አላደረግንም! እነሆ፥ ዛሬ ታላቅ የምሥራች አግኝተናል፤ ይህንንም መልካም ዜና ደብቀን ልናስቀር አይገባንም! ይህን የምሥራች ሳንነግር እስኪ ነጋ ብንቆይ በእርግጥ ቅጣት ይደርስብናል፤ ስለዚህም አሁኑኑ ሄደን ለንጉሡ የጦር መኰንኖች እንንገር!”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህም በኋላ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “መልካም አላደረግንም! እነሆ፥ ዛሬ ታላቅ የምሥራች አግኝተናል፤ ይህንንም መልካም ዜና ደብቀን ልናስቀር አይገባንም! ይህን የምሥራች ሳንነግር እስኪነጋ ብንቈይ በእርግጥ ቅጣት ይደርስብናል፤ ስለዚህም አሁኑኑ ሄደን ለንጉሡ የጦር መኰንኖች እንንገር!”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከዚ​ያም ወዲያ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “መል​ካም አላ​ደ​ረ​ግ​ንም፤ ዛሬ የመ​ል​ካም ምሥ​ራች ቀን ነው፤ እኛ ዝም ብለ​ናል፤ እስ​ኪ​ነ​ጋም ድረስ ብን​ቆይ በደ​ለ​ኞች እን​ሆ​ና​ለን፤ ኑ፥ እን​ሂድ፤ ለን​ጉሥ ቤተ​ሰ​ብም እን​ና​ገር” ተባ​ባሉ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 7:9
14 交叉引用  

ንዕማንም ገብቶ ለጌታው “ከእስራኤል አገር የሆነች አንዲት ብላቴና እንዲህና እንዲህ ብላለች፤” ብሎ ነገረው።


መጥተውም “ወደ ሶርያውያን ሰፈር መጣን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ሰው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም፤” ብለው ወደ ከተማይቱ ደጅ ጠባቂ ጮኹ።


በበሩም መግቢያ አራት ለምጻም ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በርሳቸውም “እስክንሞት ድረስ በዚህ ለምን እንቀመጣለን?


እግዚአብሔር ለሶርያውያን የሠረገላና የፈረስ የብዙም ጭፍራ ድምፅ አሰምቶ ነበር፤ እርስ በርሳቸውም “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ የኬጢያውያንና የግብጻውያንን ነገሥታት ቀጥሮ አምጥቶብናል፤” ይባባሉ ነበር።


እነዚህም ለምጻሞች ወደ ሰፈሩ መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ ወደ አንድ ድንኳን ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም ወርቅና ብር ልብስም ወሰዱ፤ ሄደውም ሸሸጉት፤ ተመልሰውም ወደ ሌላ ድንኳን ገቡ፤ ከዚያም ደግሞ ወስደው ሸሸጉ።


በመጀመሪያ ለጽዮን፦ እነኋቸው እላለሁ፥ ለእየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።


የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።


እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኃጢአታችሁም እንዲያገኛችሁ እወቁ።


መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤


እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።


跟着我们:

广告


广告