Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከባሪያዎቹም አንዱ መልሶ “በከተማ ከቀሩት ፈረሶች አምስት ይውሰዱ፤ እነሆ፥ እንደ ቀሩት እንደ እስራኤል ወገን ሁሉ ናቸው፤ እነሆ፥ እንዳለቁ እንደ እስራኤል ወገን ሁሉ ናቸው፤ እንስደድም፤ እንይም፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከጦር አለቆቹም አንዱ እንዲህ አለ፤ “ጥቂት ሰዎች በከተማዪቱ ውስጥ ከተረፉት ፈረሶች ዐምስቱን ይዘው ይሂዱ፤ ዕጣ ፈንታቸውም በዚህ ከቀሩት እስራኤላውያን ሁሉ ዕድል ጋራ አንድ ነው፤ የሚጠብቃቸው ቢኖር በዚህ በሙሉ እንዳለቁት እስራኤላውያን መሆን ብቻ ነው፤ ስለዚህ እንላካቸውና የሆነውን እንይ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከባለሟሎቹም አንዱ “በዚህች ከተማ ውስጥ የተረፈው ሕዝብ ከዚህ በፊት እንደ ሞቱት ሰዎች ሁሉ ከሞት የሚያመልጥ አይደለም፤ ስለዚህ የሆነውን ነገር ማወቅ እንድንችል ጥቂት ሰዎችን መርጠን ከሞት ከተረፉት አምስት ፈረሶች ጋር እንላክ” ሲል ሐሳብ አቀረበ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከባለሟሎቹም አንዱ “በዚህች ከተማ ውስጥ የተረፈው ሕዝብ ከዚህ በፊት እንደ ሞቱት ሰዎች ሁሉ ከሞት የሚያመልጥ አይደለም፤ ስለዚህ የሆነውን ነገር ማወቅ እንድንችል ጥቂት ሰዎችን መርጠን ከሞት ከተረፉት አምስት ፈረሶች ጋር እንላክ” ሲል ሐሳብ አቀረበ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እዚህ ከቀ​ሩት ፈረ​ሶች አም​ስት ይው​ሰዱ፤ እነሆ፥ እነ​ርሱ በቀ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቍጥር ናቸው፥ እን​ስ​ደ​ድና ይዩ” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 7:13
7 交叉引用  

ባሪያዎቹም ቀርበው “አባት ሆይ! ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ ‘ታጠብና ንጹሕ ሁን፤’ ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት።


ሲናገራቸውም መልእክተኛው ወደ እርሱ ደረሰ፤ እርሱም “እነሆ፥ ይህ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ እግዚአብሔርን ገና እጠብቅ ዘንድ ምንድር ነኝ?” አለ።


ንጉሡም በሌሊት ተነሥቶ ባሪያዎቹን “ሶርያውያን ያደረጉብንን እነግራችኋለሁ፤ እንደ ተራብን ያውቃሉ፤ ስለዚህ ‘ከከተማይቱ በወጡ ጊዜ በሕይወታቸው እንይዛቸዋለን፤ ወደ ከተማም እንገባለን፤’ ብለው በሜዳ ይሸሸጉ ዘንድ ከሰፈሩ ወጥተዋል፤” አላቸው።


ሁለትም ሠረገሎች ከፈረሶች ጋር ወሰዱ፤ ንጉሡም “ሄዳችሁ እዩ፤” ብሎ ከሶርያውያን ሠራዊት በኋላ ላከ።


ወደ ከተማ እንገባ ዘንድ ብንወድድ ራብ በከተማ አለ፤ በዚያም እንሞታለን፤ በዚህም ብንቀመጥ እንሞታለን። እንግዲህ ኑ፤ ወደ ሶርያውያን ሰፈር እንሽሽ፤ በሕይወት ቢያኖሩን እንኖራለን፤ ቢገድሉንም እንሞታለን፤” ተባባሉ።


ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ፥ በሰይፍ የሞቱ አሉ፥ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ፥ በራብ የከሱ አሉ፥ ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋልና።


ጤት። በሰይፍ የሞቱ በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፥ እነዚህ የምድርን ፍሬ አጥተው ተወግተውም ቀጥነዋል።


跟着我们:

广告


广告