Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 6:31 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ንጉሡም “የሣፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ዛሬ በላዩ ያደረ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ! ይህንም ይጨምርብኝ!” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ንጉሡም፣ “የሣፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ዛሬ በዐንገቱ ላይ ካደረ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ዛተ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ንጉሡም ድምፁን ከፍ በማድረግ “የዛሬይቱ ጀንበር ከመጥለቅዋ በፊት የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ሳይቆረጥ ቢያድር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ!” ሲል ተናገረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ንጉሡም ድምፁን ከፍ በማድረግ “የዛሬይቱ ጀንበር ከመጥለቅዋ በፊት የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ሳይቈረጥ ቢያድር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ!” ሲል ተናገረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ንጉ​ሡም፥ “የሣ​ፋጥ ልጅ የኤ​ል​ሳዕ ራስ ዛሬ በላዩ ያደረ እንደ ሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ያድ​ር​ገኝ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ለኝ” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 6:31
18 交叉引用  

ለአሜሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።


ሕዝቡም ሁሉ ገና ሳይመሽ ዳዊትን እንጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋብዙት መጡ፥ ዳዊት ግን፦ ፀሐይ ሳትጠልቅ እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፥ ይህንም ይጨምርብኝ ብሎ፥ ማለ።


መንግሥትን ከሳኦል ቤት ያወጣ ዘንድ የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረው ከፍ ያደርግ ዘንድ


አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ “እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?” አለው።


ኤልዛቤልም “ነገ በዚህ ጊዜ ነፍስህን ከእነዚህ እንደ አንዲቱ ነፍስ ባላደርጋት፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ፤ ይህንም ይጨምሩብኝ፤” ብላ ወደ ኤልያስ መልእክተኛ ላከች።


ንጉሡም ሰሎሞን “አዶንያስ ይህን ቃል በሕይወቱ ላይ አለመናገሩ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ።


ሁለትም ምናምንቴ ሰዎች በፊቱ አስቀምጡና ‘እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል፤’ ብለው ይመስክሩበት፤ አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ ውገሩት፤” ብላ ጻፈች።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም ትንቢት አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ፤” አለው። ኢዮሣፍጥም “ንጉሥ እንዲህ አይበል፤” አለ።


የእግዚአብሔርም ሰው ሎሌ ግያዝ “ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፤ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተ ኋለው እሮጣለሁ፤ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ፤” አለ።


አለቆቹም ንጉሡን፦ ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚህች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፥ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና አሉት።


ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም” አላቸው።


በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፤ በዚያም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ እንዲሁም ይጨምርብኝ፤” አለች።


ሳኦልም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብኝ እንዲህም ይጨምርብኝ፥ ዮናታን ሆይ፥ ፈጽመህ ትሞታለህ አለ።


ለእርሱም ከሆነው ሁሉ እስከ ነገ ጥዋት ድረስ አንድ ወንድ ስንኳ ብተው እግዚአብሔር በዳዊት ላይ እንዲህ ያድርግ እንዲህም ይጨምር ብሎ ነበር።


እርሱም፦ እግዚአብሔር የነገረህ ነገር ምንድር ነው? ከእኔ አትሸሽግ፥ ከነገረህ ነገር ሁሉ የሸሸግኽኝ እንደ ሆነ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግብህ፥ እንዲህም ይጨምርብህ አለው።


跟着我们:

广告


广告