Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 6:29 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ልጄንም ቀቅለን በላነው፤ በማግሥቱም ‘እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤’ አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው፤” ብላ መለሰችለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ስለዚህ ልጄን ቀቅለን በላነው። በማግስቱም፣ ‘እንድንበላው ልጅሽን አምጪው’ አልኋት፤ እርሷ ግን ደበቀችው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ስለዚህም የእኔን ልጅ ቀቅለን በላን፤ በማግስቱም ‘ልጅሽን አምጪና እንብላ’ ብዬ ጠየቅኋት፤ እርሷ ግን ደበቀችው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ስለዚህም የእኔን ልጅ ቀቅለን በላን፤ በማግስቱም ‘ልጅሽን አምጪና እንብላ’ ብዬ ጠየቅኋት፤ እርስዋ ግን ደበቀችው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ልጄ​ንም ቀቅ​ለን በላ​ነው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም፦ እን​ድ​ን​በ​ላው ልጅ​ሽን አምጪ አል​ኋት፤ ልጅ​ዋ​ንም ሸሸ​ገ​ችው” ብላ መለ​ሰ​ች​ለት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 6:29
9 交叉引用  

ደኅነኛውም የነበራት ሴት አንጀትዋ ስለ ልጅዋ ናፍቆአልና “ጌታዬ ሆይ! ደኀነኛውን ለእርስዋ ስጣት እንጂ አትግደል፤” ብላ ለንጉሡ ተናገረች። ያችኛይቱ ግን “ይከፈል እንጂ ለእኔም ለአንቺም አይሁን፤” አለች።


በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።


እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።


ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው።


እስከዚህም ድረስ ባትሰሙኝ፥ በእንቢተኝነትም ብትሄዱብኝ፥


የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።


በአገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ደጆች ሁሉ ከብበው ያስጭንቁሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ በደጆች ሁሉ ከብበው ያስጨንቁሃል።


ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።


በወንድና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች፤ በደጆችህም ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሁሉን ስላጣች በስውር ትበላቸዋለች።


跟着我们:

广告


广告