Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 6:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከባሪያዎቹም አንዱ “ጌታዬ ሆይ! እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከጦር አለቆቹም አንዱ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ከእኛ በኩል ማንም ሰው የለም፤ ነገር ግን አንተ በእልፍኝህ ሆነህ እንኳ የምትናገረውን አንዲቱም ሳትቀር ለእስራኤል ንጉሥ የሚነግረው በእስራኤል ያለው ነቢዩ ኤልሳዕ ነው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከእነርሱም አንዱ “ንጉሥ ሆይ፥ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው” ሲል መለሰለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 6:12
19 交叉引用  

እርሱም “ያ ሰው ከሠረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? ብሩንና ልብሱን፥ የወይራውንና የወይኑን ቦታ፥ በጎችንና በሬዎችን፥ ወንዶችንና ሴቶችን ባሪያዎች ትቀበል ዘንድ ይህ ጊዜው ነውን?


እመቤትዋንም “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር፤” አለቻት።


የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ “ልብስህን ለምን ቀደድህ? ወደ እኔ ይምጣ፤ በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ እንዳለ ያውቃል፤” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።


የሶርያም ንጉሥ ልብ ስለዚህ እጅግ ታወከ፤ ባሪያዎቹንም ጠርቶ “ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ አትነግሩኝምን?” አላቸው።


እርሱም “ልኬ አስይዘው ዘንድ ሄዳችሁ ወዴት እንደሆነ እዩ፤” አለ። እነርሱም “እነሆ፥ በዶታይን አለ፤” ብለው ነገሩት።


ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ባሪያዎችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ምድጆችህም፥ ወደ ቡሃቃዎችህም ይገባሉ፤


የሰማይ ወፍ ቃሉን ይወስደዋልና፥ ባለ ክንፎችም ነገሩን ይናገራሉና በልብህ አሳብ እንኳ ቢሆን ንጉሥን አትስደብ፥ በመኝታ ቤትህም ባለጠጋን አትስደብ።


ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው!


ተመካከሩ፥ ምክራችሁ ይፈታል፥ ቃሉን ተናገሩ፥ ቃሉም አይጸናም፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ንጉሡም ዳንኤልን፦ ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታትም ጌታ፥ ምሥጢርም ገላጭ ነው ብሎ ተናገረው።


በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።


跟着我们:

广告


广告