Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ “ልብስህን ለምን ቀደድህ? ወደ እኔ ይምጣ፤ በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ እንዳለ ያውቃል፤” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ፣ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን መቅደዱን በሰማ ጊዜ፣ እንዲህ ሲል ላከበት፤ “ልብስህን ለምን ቀደድህ? ሰውየው ወደ እኔ ይምጣ፤ ከዚያም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን ያውቃል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ነቢዩ ኤልሳዕም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ መልእክት ልኮ “ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እኔም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን አሳየዋለሁ!” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ነቢዩ ኤልሳዕም የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ መልእክት ልኮ “ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እኔም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን አሳየዋለሁ!” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ልብ​ሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፥ “ልብ​ስ​ህን ለምን ቀደ​ድህ? ንዕ​ማን ወደ እኔ ይምጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ነቢይ እን​ዳለ ያው​ቃል” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 5:8
14 交叉引用  

ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፦ ልብሳችሁን ቅደዱ፥ ማቅም ልበሱ፥ በአበኔርም ፊት አልቅሱ አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ።


የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ


ሴቲቱም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በአፍህ እውነት እንደ ሆነ አሁን አወቅሁ፤” አለችው።


እነርሱም “አንድ ሰው ሊገናኘን መጣና ‘ሂዱ፤ ወደ ላካችሁም ንጉሥ ተመልሳችሁ” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ የላከህ በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤” በሉት፤’ አለን፤” አሉት።


እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ፤ አሁንም ከባሪያህ ገጸ በረከት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ፤” አለ።


እመቤትዋንም “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር፤” አለቻት።


የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ “ሰውን ከለምጹ እፈውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስደዱ እኔ በውኑ ለመግደልና ለማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነውን? ተመልከቱ፤ የጠብ ምክንያትም እንደሚፈልግብኝ እዩ፤” አለ።


ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፤ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ።


እነዚህም ባሪያዎችህ ሁሉ፥ አንተ ውጣ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።’” ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።


እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ።


ያዕቆብ ወደ ሶርያ አገር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም ጠባቂ ነበረ።


ለእናንተም ለአሕዛብ እናገራለሁ። እኔ የአሕዛብ ሐዋርያ በሆንሁ መጠን ሥጋዬ የሆኑትን አስቀንቼ ምናልባት ከእነርሱ አንዳንዱን አድን እንደሆነ አገልግሎቴን አከብራለሁ።


እርሱም፦ እነሆ፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በዚህች ከተማ አለ፥ እርሱም የተከበረ ሰው ነው፥ የሚናገረውም ሁሉ በእውነት ይፈጸማል፥ አሁን ወደዚያ እንሂድ፥ ምናልባት የምንሄድበትን መንገድ ይነግረናል አለው።


跟着我们:

广告


广告