Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ባሪያዎቹም ቀርበው “አባት ሆይ! ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር፤ ይልቁንስ ‘ታጠብና ንጹሕ ሁን፤’ ቢልህ እንዴት ነዋ!” ብለው ተናገሩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የንዕማን አገልጋዮች ግን ወደ እርሱ ቀርበው፣ “አባት ሆይ፤ ነቢዩ ከዚህ ከበድ ያለ ነገር እንድታደርግ ቢነግርህ ኖሮ አታደርገውም ነበርን? ታዲያ፣ ‘ታጠብና ንጻ’ ቢልህ ምኑ አስቸገረህ?” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ወደ እርሱ መጥ​ተው፥ “ነቢዩ ታላቅ ነገር ቢነ​ግ​ርህ ባደ​ረ​ግ​ኸው ነበር፤ ይል​ቁ​ንስ፦ ተጠ​መ​ቅና ንጹሕ ሁን ቢልህ እን​ዴት ነዋ!” ብለው ተና​ገ​ሩት።

参见章节 复制




2 ነገሥት 5:13
31 交叉引用  

የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው አዋጅ ነጋሪም፦ ስገዱ እያለ በፊት በፊት ይጮኽ ነበር እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ።


ደግሞ እግዚአብሔር ስለ ኤልዛቤል ‘በኢይዝራኤል ቅጥር አጠገብ ኤልዛቤልን ውሾች ይበሉአታል፤’ ብሎ ተናገረ።


ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች፤” አለ።


ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ አባቴ ሆይ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ተረተረው።


ኤልሳዕም “ሂድ፤ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ፤” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ።


እመቤትዋንም “ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር፤” አለቻት።


የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ አልሳዕን “አባቴ ሆይ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን?” አለው።


አዛሄልም ሊገናኘው ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ከደማስቆ መልካሙን ነገር ሁሉ የአርባ ግመል ጭነት ገጸ በረከት ወሰደ፤ መጥቶም በፊቱ ቆመና “ልጅህ የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ሲል ወደ አንተ ልኮኛል፤” አለ።


ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፥ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፥


እናንተ ስሜን የምታቃልሉ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባሪያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተም፦ ስምህን ያቃለልን በምንድር ነው? ብላችኋል።


አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ።


ጴጥሮስም፦ “የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም” አለው። ኢየሱስም፦ “ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም” ብሎ መለሰለት።


“ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ” አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።


አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።


በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።


ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤


በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤


ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቅት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤


እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ አልሁት። አለኝም፦ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ።


ደግሞም፥ አባቴ ሆይ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ እወቅ፥ የልብስህንም ዘርፍ በቆረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፥ ስለዚህም በእጄ ክፋትና በደል እንደሌለ፥ አንተም ነፍሴን ልትወስድ ምንም ብታሳድደኝ እንዳልበደልሁህ ተመልክተህ እወቅ።


እርሱ ግን፦ አልበላም ብሎ እንቢ አለ፥ ነገር ግን ባሪያዎቹና ሴቲቱ አስገደዱት፥ ቃላቸውንም ሰማ ከምድርም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ።


ሳኦልም ብላቴናውን፦ የተናገረኸው ነገር መልካም ነው፥ ና፥ እንሂድ አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ።


跟着我们:

广告


广告