Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:40 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ሰዎቹም ይበሉ ዘንድ ቀዱ፤ ወጡንም በቀመሱ ጊዜ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! በምንቸቱ ውስጥ ሞት አለ፤” ብለው ጮኹ፤ ይበሉም ዘንድ አልቻሉም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ሰዎቹ እንዲመገቡትም ወጡ ወጣ፤ ገና አንደ ቀመሱትም፣ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ በምንቸቱ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ነቢያትም እንዲመገቡት የወጣላቸውን ወጥ ቀምሰው “በዚህ ወጥ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ወደ ኤልሳዕ ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ነቢያትም እንዲመገቡት የወጣላቸውን ወጥ ቀምሰው “በዚህ ወጥ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ወደ ኤልሳዕ ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ከዚ​ህም በኋላ ሰዎቹ ይበሉ ዘንድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የበ​ሰ​ለ​ው​ንም ቅጠል በሚ​በ​ሉ​በት ጊዜ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ በም​ን​ቸቱ ውስጥ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ፤ ይበ​ሉም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:40
11 交叉引用  

ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤


እርስዋም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።


ደግሞም ሌላ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ላከበት፤ እርሱም “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ‘ፈጥነህ ውረድ’ ይላል፤” ብሎ ተናገረ።


ደግሞም ሦስተኛ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፤ ሦስተኛውም የአምሳ አለቃ ወጥቶ በኤልያስ ፊት በጕልበቱ ተንበረከከና “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ነፍሴና የእነዚህ የአምሳው ባሪያዎችህ ነፍስ በፊትህ የከበረች ትሁን።


ንጉሡም የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፤ ወደ እርሱም ወጣ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርሱም “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ‘ውረድ’ ይልሃል፤” አለው።


አንዱም ቅጠላቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ የምድረ በዳውንም ሐረግ አገኘ፤ ከዚያም የበረሃ ቅል ሰበሰበ፤ ልብሱንም ሞልቶ ተመለሰ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም።


ለባልዋም “ይህ በእኛ ዘንድ ሁልጊዜ የሚያልፈው ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆነ አውቃለሁ።


አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው፤”


ወደ ማራም በመጡ ጊዜ የማራ ውኃ መራራ ነበረና ሊጠጡ አልቻሉም፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም ማራ ተብሎ ተጠራ።


የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።


የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት።


跟着我们:

广告


广告