Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:39 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 አንዱም ቅጠላቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ የምድረ በዳውንም ሐረግ አገኘ፤ ከዚያም የበረሃ ቅል ሰበሰበ፤ ልብሱንም ሞልቶ ተመለሰ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከእነርሱም አንዱ ቅጠላ ቅጠል ለማምጣት ወደ ሜዳ ወጥቶ፤ ዱር በቀል ሐረግ አገኘ፤ ከሐረጉም ላይ የቅል ፍሬ ለቅሞ በልብሱ ሙሉ ይዞ ተመለሰና ቈራርጦ በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን ማንም አላወቀም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቈርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 አን​ዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በም​ድረ በዳ​ውም የወ​ይን ቦታ አገኘ፤ ከዚ​ያም የም​ድር ቅጠላ ቅጠል ሰብ​ሰበ፤ ልብ​ሱ​ንም ሞላ፤ መት​ሮም በወጡ ምን​ቸት ውስጥ ጨመ​ረው፤ አበ​ሰ​ለ​ውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላ​ወ​ቁም።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:39
9 交叉引用  

ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤


የቤቱንም ውስጥ በተጎበጎበና በፈነዳ አበባ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።


ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልገላ መጣ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ሎሌውንም “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያት ልጆችም ወጥ ሥራ፤” አለው።


ሰዎቹም ይበሉ ዘንድ ቀዱ፤ ወጡንም በቀመሱ ጊዜ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! በምንቸቱ ውስጥ ሞት አለ፤” ብለው ጮኹ፤ ይበሉም ዘንድ አልቻሉም።


ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ስተማመን ስለምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?


እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፥ አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?


እርሱ ግን መልሶ፦ የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።


የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥


跟着我们:

广告


广告