Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:27 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወደ ተራራው ወደ እግዚአብሔር ሰው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ጨበጠች፤ ግያዝም ሊያርቃት ቀረበ፤ የእግዚአብሔርም ሰው “ነፍስዋ አዝናለችና ተዋት፤ እግዚአብሔርም ያንን ከእኔ ሰውሮታል፤ አልነገረኝምም፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ተራራ ስትደርስም እግሩ ላይ ተጠመጠመች፤ ግያዝ ሊያስለቅቃት ሲመጣ፣ የእግዚአብሔር ሰው ግን፣ “እጅግ ዐዝናለችና ተዋት! እግዚአብሔር ይህን ለምን ከእኔ እንደ ሰወረውና እንዳልነገረኝ አልገባኝም” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርሷ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርስዋ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:27
19 交叉引用  

እግዚአብሔርም አለ፤ እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን?


ናታንም ንጉሡን፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ሂድ፥ በልብህም ያለውን ሁሉ አድርግ አለው።


እንዲሁም ሄደች፤ ወደ እግዚአብሔርም ሰው ወደ ቀርሜሎስ ተራራ መጣች። የእግዚአብሔርም ሰው ከሩቅ ባያት ጊዜ ሎሌውን ግያዝን “እነኋት ሱነማዊቲቱ መጣች፤


ትቀበላትም ዘንድ ሩጥና ‘በደኅናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅሽስ ደኅና ነውን?’ በላት፤” አለው። እርስዋም “ደኅና ነው፤” አለች።


ከባሪያዎቹም አንዱ “ጌታዬ ሆይ! እንዲህ እኮ አይደለም፤ ነገር ግን በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል፤” አለ።


ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት፥ የኀዘን እንጕርጕሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።


በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።


እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።


ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን እያሉ አብዝተው ጮኹ።


እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና፦ ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።


እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው።


ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።


በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።


ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።


በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን፦ ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም፦ ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።


እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር፥ በእግዚአብሔርም ፊት ጸለየች፥ ጽኑ ልቅሶም አለቀሰች።


跟着我们:

广告


广告