Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ትቀበላትም ዘንድ ሩጥና ‘በደኅናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅሽስ ደኅና ነውን?’ በላት፤” አለው። እርስዋም “ደኅና ነው፤” አለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በል ሩጠህ ሂድና፣ ‘ምነው ደኅና አይደለሽምን? ባልሽ ደኅና አይደለምን? ልጅሽስ ደኅና አይደለምን?’ ብለህ ጠይቃት።” እርሷ፣ “ሁሉ ነገር ደኅና ነው” አለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ፈጠን ብለህ ሂድና የእርሷን፥ የባሏንና የልጇን ደኅንነት ጠይቃት” አለው። እርሷም ግያዝን “ሁላችንም ደኅና ነን” ስትል ነገረችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ፈጠን ብለህ ሂድና የእርስዋን፥ የባልዋንና የልጅዋን ደኅንነት ጠይቃት” አለው። እርስዋም ግያዝን “ሁላችንም ደኅና ነን” ስትል ነገረችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አሁ​ንም ሩጥና ተቀ​በ​ላት፤ በደ​ኅ​ናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅ​ሽስ ደኅና ነውን? በላት” አለው። እር​ስ​ዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:26
16 交叉引用  

እርሱ፦ ደኅና ነው? አላቸው እነርሱም፦ አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት።


እርሱም፦ ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅን እንደ ሆኑ እይ ወሬአቸውንም አምጣክኝ አለው። እንዲንም ከኬብሮን ቆላ ሰደደው ወደ ሴኬምም መጣ።


እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው እንዲህም አለ፦ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን?


ንጉሡም፦ ብላቴናው አቤሴሎም ደህና ነውን? አለ። አኪማአስም፦ ኢዮአብ እኔን ባሪያህንና የንጉሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ትልቅ ሽብር አይቻለሁ፥ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም ብሎ መለሰለት።


እርሱም “መባቻ ወይም ሰንበት ያይደለ ዛሬ ለምን ትሄጂበታለሽ?” አለ። እርስዋም “ደኅና ነው” አለች።


እንዲሁም ሄደች፤ ወደ እግዚአብሔርም ሰው ወደ ቀርሜሎስ ተራራ መጣች። የእግዚአብሔርም ሰው ከሩቅ ባያት ጊዜ ሎሌውን ግያዝን “እነኋት ሱነማዊቲቱ መጣች፤


ወደ ተራራው ወደ እግዚአብሔር ሰው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ጨበጠች፤ ግያዝም ሊያርቃት ቀረበ፤ የእግዚአብሔርም ሰው “ነፍስዋ አዝናለችና ተዋት፤ እግዚአብሔርም ያንን ከእኔ ሰውሮታል፤ አልነገረኝምም፤” አለ።


እርሱም “ደኅና ነው፤ ‘አሁን ከነቢያት ወገን የሆኑት ሁለት ጕልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋል፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ፤’ ብሎ ጌታዬ ላከኝ፤” አለ።


ሙሴም አሮንን፦ እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች።


ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፦ “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው።


ይህንም አሥሩን አይብ ወደ ሻለቃው ውሰደው፥ የወንድሞችህንም ደኅንነት ጠይቅ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ።


ሳሙኤልም ነገሩን ሁሉ ነገረው፥ አንዳችም አልሸሸገውም። ዔሊም፦ እርሱ እግዚአብሔር ነው፥ ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ።


跟着我们:

广告


广告