Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እንዲሁም ሄደች፤ ወደ እግዚአብሔርም ሰው ወደ ቀርሜሎስ ተራራ መጣች። የእግዚአብሔርም ሰው ከሩቅ ባያት ጊዜ ሎሌውን ግያዝን “እነኋት ሱነማዊቲቱ መጣች፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ስለዚህ ተነሥታ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደች። የእግዚአብሔር ሰው በሩቁ ሲያያት አገልጋዩን ግያዝን እንዲህ አለው፤ “ሱነማዪቱን አየሃት፤ ያቻትና!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እርሷም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደ ነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች። ኤልሳዕም ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን “ተመልከት! ያቺ ሴት ከሱነም ወደዚህ በመምጣት ላይ ናት!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እርስዋም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች። ኤልሳዕም ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን “ተመልከት! ያቺ ሴት ከሱነም ወደዚህ በመምጣት ላይ ናት!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እን​ዲ​ሁም ሄደች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ወጣች። ኤል​ሳ​ዕም ያችን ሴት ወደ እርሱ ስት​መጣ ባያት ጊዜ ሎሌ​ውን ግያ​ዝን፥ “እነ​ኋት፥ ሱማ​ና​ዊት መጣች፤

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:25
10 交叉引用  

አሁንም ልከህ እስራኤልን ሁሉ፥ በኤልዛቤልም ማዕድ የሚበሉትን አራት መቶ አምሳ የበኣልን ነቢያት፥ አራት መቶም የማምለኪያ ዐፀድን ነቢያት ወደ እኔ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብ፤” አለ።


አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ፤ ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጉልበቱ መካከል አድርጎ በግምባሩ ተደፋ።


ንጉሡም የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ሰደደ፤ ወደ እርሱም ወጣ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ ነበር። እርሱም “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ‘ውረድ’ ይልሃል፤” አለው።


ከዚያም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።


አህያውንም አስጭና ሎሌዋን “ንዳ፤ ሂድ፤ እኔ ሳላዝዝህ አታዘግየኝ፤” አለችው።


ትቀበላትም ዘንድ ሩጥና ‘በደኅናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅሽስ ደኅና ነውን?’ በላት፤” አለው። እርስዋም “ደኅና ነው፤” አለች።


ወደ ተራራው ወደ እግዚአብሔር ሰው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ጨበጠች፤ ግያዝም ሊያርቃት ቀረበ፤ የእግዚአብሔርም ሰው “ነፍስዋ አዝናለችና ተዋት፤ እግዚአብሔርም ያንን ከእኔ ሰውሮታል፤ አልነገረኝምም፤” አለ።


የእግዚአብሔርም ሰው ሎሌ ግያዝ “ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፤ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተ ኋለው እሮጣለሁ፤ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ፤” አለ።


ንጉሡም ከእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ከግያዝ ጋር “ኤልሳዕ ያደረገውን ተአምራት ሁሉ ንገረኝ፤” እያለ ይጫወት ነበር።


እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፥ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፥ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።


跟着我们:

广告


广告