Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርሱም “እንግዲህ ምን እናድርግላት?” አለ። ግያዝም “ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሸምግሎአል፤” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኤልሳዕም፣ “ታዲያ ምን ይደረግላት” ሲል ጠየቀ። ግያዝም፣ “ልጅ እኮ የላትም፤ ባሏም ሸምግሏል” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባሏም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እር​ሱም ግያ​ዝን፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?” አለው። ሎሌው ግያ​ዝም፤ “ልጅ የላ​ትም፥ ባል​ዋም ሸም​ግ​ሎ​አል” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:14
11 交叉引用  

አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ፥ የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልን? ዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?


ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ መካን ነበረችና፤ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች።


ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት፤ ያቆብንም፦ ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው።


በጠራትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። እርሱም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ አሳብ አሰብሽልኝ፤ አሁንስ ምን ላድርግልሽ? ለንጉሥ ወይስ ለሠራዊት አለቃ ልንገርልሽን? በላት፤” አለው፤ እርስዋም “እኔ በወገኔ መካከል ተቀምጫለሁ፤” ብላ መለሰች።


እርሱም “ጥራት” አለ። በጠራትም ጊዜ በደጃፉ ቆመች።


ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።


ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፥ ሚስቱም መካን ነበረች፥ ልጅም አልወለደችም።


ሁለትም ሚስቶች ነበሩት የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ፥ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፥ ለሐና ግን ልጅ አልነበራትም።


ባልዋም ሕልቃና፦ ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሺም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን? አላት።


跟着我们:

广告


广告