Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 4:13 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በጠራትም ጊዜ በፊቱ ቆመች። እርሱም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ አሳብ አሰብሽልኝ፤ አሁንስ ምን ላድርግልሽ? ለንጉሥ ወይስ ለሠራዊት አለቃ ልንገርልሽን? በላት፤” አለው፤ እርስዋም “እኔ በወገኔ መካከል ተቀምጫለሁ፤” ብላ መለሰች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኤልሳዕም፣ “ ‘ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል፤ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊአለሽ? ለንጉሡ ወይስ ለሰራዊቱ አዛዥ የምንነግርልሽ ጕዳይ አለን?’ ብለህ ጠይቃት” አለው። ሴቲቱም መልሳ፣ “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ግያዝ “ለእኛ ስላደረገችው መልካም ነገር ሁሉ ምን አደርግላት ዘንድ እንደምትፈልግ ጠይቃት፤ ምናልባት ወደ ንጉሡ ወይም ወደ ጦር አዛዡ ዘንድ ሄጄ የምነግርላት ጉዳይ ሊኖር ይችላል” አለው። እርሷም “በዘመዶች መካከል በምኖርበት በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም” ስትል መለሰችለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ግያዝ “ለእኛ ስላደረገችው መልካም ነገር ሁሉ ምን አደርግላት ዘንድ እንደምትፈልግ ጠይቃት፤ ምናልባት ወደ ንጉሡ ወይም ወደ ጦር አዛዡ ዘንድ ሄጄ የምነግርላት ጉዳይ ሊኖር ይችላል” አለው። እርስዋም “በዘመዶች መካከል በምኖርበት በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም” ስትል መለሰችለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ክብር አከ​በ​ር​ሽኝ ምን ላድ​ር​ግ​ልሽ? ለን​ጉሥ ወይስ ለሠ​ራ​ዊት አለቃ የም​ነ​ግ​ር​ልሽ ጉዳይ እን​ዳ​ለሽ በላት” አለው፤ እር​ስ​ዋም፥ “እኔ በወ​ገኔ መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ” ብላ መለ​ሰች።

参见章节 复制




2 ነገሥት 4:13
22 交叉引用  

ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ ቢሆን ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ፤ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።


ለአሜሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቁራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።


አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ከእርሱ የሚሻሉትን ሁለቱን ጻድቃን ሰዎች፥ የእስራኤልን ሠራዊት አለቃ የኔርን ልጅ አበኔርን፥ የይሁዳንም ሠራዊት አለቃ የዬቴርን ልጅ አሜሳይን፥ በሰይፍ ገድሎአልና እግዚአብሔር ደሙን በራሱ ላይ ይመልሰው።


ሎሌውንም ግያዝን “ይህችን ሱነማዊት ጥራ፤” አለው።


እርሱም “እንግዲህ ምን እናድርግላት?” አለ። ግያዝም “ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሸምግሎአል፤” ብሎ መለሰ።


ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሥላትን ሴት “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር ራብ ጠርቶአል፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይመጣል፤” ብሎ ተናገራት።


በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ መልእክት አለኝ፤” አለ። ኢዩም “ለማንኛችን ነው?” አለ። እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ ነው፤” አለ።


ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።


ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።


跟着我们:

广告


广告