Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 3:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከተሞችንም አፈረሱ፤ በመልካሞቹም እርሻዎች ሁሉ ላይ እስኪሞሉ ድረስ እያንዳንዱ ሰው አንድ አንድ ድንጋይ ይጥል ነበር፤ የውሃውንም ምንጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የሚያፈሩትንም ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ የቂርሐራሴትን ድንጋዮች ብቻ አስቀሩ፤ ባለ ወንጭፎች ግን ከብበው መቱአት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከተሞቹን ደመሰሱ፤ መልካሙን የዕርሻ መሬት ሁሉ እስኪሸፍነው ድረስ፣ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ድንጋይ ጣለበት፤ ምንጮቹን በሙሉ ደፈኑ፤ ጥሩ ጥሩውንም ዛፍ ሁሉ ቈርጠው ጣሉ። ቂርሐራሴት ብቻ ከነድንጋይዋ ቀርታ ነበር፤ እርሷንም ቢሆን ባለወንጭፉ ሰራዊት ከብቦ አደጋ ጣለባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቆረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርሷንም ድንጋይ የሚያወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቈረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርስዋንም ድንጋይ የሚያወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 3:25
16 交叉引用  

በአባቱ በአብርሃም ዘመን የአባቱ ሎሌዎች የማሱአቸውን ጕድጓዶች ሁሉ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑአቸው አፈርንም ሞሉባቸው።


ይስሐቅም በአባቱ በአብርሃም ዘመን ቈፍረዋቸ የነበሩትን የውኃ ጕድጓዶች ደግሞ አስቈፈረ፤ አብርሃም ከሞተ በኍላ የፍልስጥኤም ሰዎች ደፍነዋቸው ነበሩን አባቱም ይጠራቸው በነብረው ስም ጠራቸው።


ሞዓብን መታ፥ ሞዓባውያንንም በምድር ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፥ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ሙሉ ለሕይወት ሰፈራቸው፥ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት።


የተመሸጉትንና ያማሩትን ከተሞች ሁሉ ትመታላችሁ፤ የሚያፈሩትንም ዛፎች ሁሉ ትቈርጣላችሁ፤ የውሃውንም ምንጮች ሁሉ ትደፍናላችሁ፤ መልካሞችንም እርሻዎች ሁሉ በድንጋይ ታበላሻላችሁ።”


ወደ እስራኤል ሰፈር በመጡ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው ሞዓባውያንን መቱ፤ እነርሱም ከፊታቸው ሸሹ፤ ሞዓባውያንንም እየመቱ ወደ አገሩ ውስጥ ገቡ።


የሞዓብም ንጉሥ ሰልፍ እንደ በረታበት ባየ ጊዜ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰባት መቶ ሰዎች ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ወደ ኤዶምያስም ንጉሥ ያልፉ ዘንድ ሞከሩ፤ አልቻሉምም።


እጅግም ሰዎች ተሰብስበው “የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ስለ ምን ያገኛሉ?” ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ወንዝ ደፈኑ።


ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም። የሞዓብ ኤር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፥ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።


ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች።


ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይ ይላል፥ ሁሉም ዋይ ይላል፥ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ።


ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ ለሞዓብም ሁሉ እጮኻለሁ፥ ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ።


ያተረፈው ትርፉ ጠፍቶበታልና፥ ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል፥ ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል።


እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓብን አትጣላ በሰልፍም አትውጋቸው።


አቤሜሌክም በዚያ ቀን ሁሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፥ ከተማይቱንም ይዞ በእርሷ የነበሩትን ሕዝብ ገደለ፥ ከተማይቱንም አፈረሰ፥ ጨውም ዘራባት።


跟着我们:

广告


广告