Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 3:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ይህም በእግዚአብሔር ዐይን ቀላል ነገር ነው፤ ደግሞም ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይህ በእግዚአብሔር ፊት ቀላል ነገር ነው። ሞዓብንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ነገር ግን ይህን ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀላል ነገር ነው፤ ከዚህም በላይ እርሱ በሞአባውያን ላይ ድልን ያጐናጽፋችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ነገር ግን ይህን ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀላል ነገር ነው፤ ከዚህም በላይ እርሱ በሞአባውያን ላይ ድልን ያጐናጽፋችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ይህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ቀላል ነገር ነውና፤ ደግ​ሞም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።

参见章节 复制




2 ነገሥት 3:18
16 交叉引用  

ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፥ ስለ ባሪያህም ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፥ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።


በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ ታናሽ ነገር መሰለው፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።


ሁለቱም ምናምንቴ ሰዎች ገብተው በፊቱ ተቀመጡ፤ ምናምንቴዎቹ ሰዎችም በሕዝቡ ፊት “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል፤” ብለው በናቡቴ ላይ መሰከሩ። የዚያን ጊዜም ከከተማ አውጥተው እስኪሞት ድረስ ወገሩት።


እነሆ፥ ክፉ ነገር አመጣብሃለሁ፤ ፈጽሞም እጠርግሃለሁ፤ ከአክዓብም በእስራኤል ዘንድ የታሰረውንና የተለቀቀውን ወንድ ሁሉ አጠፋለሁ፤


ደግሞም “አክዓብ በፊቴ እንደ ተዋረደ አየህን? በፊቴ የተዋረደ ስለ ሆነ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ፥ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም፤” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ መጣ።


ደግሞም ከነገሥታት የሚመስልህ ማንም እንዳይኖር ያልለመንኸውን ባለጠግነትና ክብር ሰጥቼሃለሁ።


ሕዝቅያስም “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨምር ቀላል ነገር ነው፤ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለስ፤” አለው።


እርሱም፦ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመልስ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።


እርሱም አለ፦ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፥ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? አምላኬን ደግሞ የምታደክሙ፥


አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ከአንተም የሚያቅት ነገር የለም።


እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፥


እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሚያደርጉትን ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ ለይሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድሪቱን በግፍ ሞልተዋታል ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፥ እነሆም፥ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫው አቅርበዋል።


ኢየሱስም ተመለከታቸውና፦ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና አለ።


ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።


እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥


跟着我们:

广告


广告