Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 25:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከተማይቱም ተሰበረች፤ ሰልፈኞችም ሁሉ በሁለት ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ሸሹ፤ ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ፤ በዓረባም መንገድ ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምንም እንኳ ባቢሎናውያን ከተማዪቱን እንደ ከበቧት ቢሆንም የከተማዪቱ ቅጥር ተጣሰ፤ ሰራዊቱም ሁሉ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ባሉት በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በዓረባ በር ዐልፎ በሌሊት ሸሸ፤ ሽሽቱም ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያያይዘው የቅጽር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተሰ​በ​ረች፤ ሰል​ፈ​ኞ​ችም ሁሉ በሁ​ለት ቅጥር መካ​ከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አት​ክ​ልት በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ በሌ​ሊት ሸሹ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ነበሩ፤ ወደ ምድረ በዳ በሚ​ወ​ስ​ደ​ውም መን​ገድ ሄዱ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 25:4
26 交叉引用  

የከለዳውያንም ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉ፤ በኢያሪኮም ሜዳ ያዙት፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ተለይተው ተበትነው ነበር።


ሰውነቱንም አጸናና፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ ሠራ።


የምጽጳም ግዛት አለቃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ከደነውም፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፥ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የሼላን መዋኛ ቅጥር ሠራ።


በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፥ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፥ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም።


አለቆችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፥ ያለ ቀስትም ተማረኩ፥ ከሩቅ ሸሽተው ከአንቺ ዘንድ የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ።


የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፥ አፍ ለአፍም ይናገረዋል፥ ዓይኑም ዓይኑን ያያል እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፥


አንተም በእርግጥ ትያዛለህ በእጅም አልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፥ ዓይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዓይን ታያለች፥ እርሱም ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይናገራል፥ ወደ ባቢሎንም ትገባለህ።


ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል አንተም ከእጃቸው አታመልጥም አለው።


በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።


ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ድምፅ የተነሣ ከተማ ሁሉ ሸሽታለች፥ ወደ ችፍግ ዱርም ይገባሉ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ፥ ከተማ ሁሉ ተለቅቃለች የሚቀመጥባትም ሰው የለም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለፈለገው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ፥ እነሆ፥ የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚፈልጉ እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።


ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፥ ለእግዚአብሔር አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።


ጋሜል። ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች፥ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፥ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት።


ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበትዋ ሁሉ ወጥቶአል፥ አለቆችዋ ማሰማርያ እንደማያገኙ ዋላዎች ሆኑ፥ ከሚያባርሩአቸው ፊት ተዳክመው ሄዱ።


በመካከላቸውም የሚኖረው አለቃ በጫንቃው ላይ አንግቶ በጨለማ ይወጣል፥ በዚያ ያወጡ ዘንድ ግንቡን ይነድላሉ፥ በዓይኑም ምድርን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።


ሊረዱትም በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ጭፍሮቹንም ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፥ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።


ቀን ለቀንም በፊታቸው እክትህን እንደ ስደተኛ እክት አውጣው፥ በማታም ጊዜ በፊታቸው ስደተኞች እንደሚወጡ እንዲሁ ውጣ።


እንዲህም ሆነ፥ በተማረክን በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማይቱ ተመታች አለኝ።


ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፥ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል፤ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።


በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፥ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።


እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፥ በሰባት መንገድ ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ ለምድርም መንግሥታት ሁሉ ድንጋጤ ትሆናለህ።


እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥ 2 እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ 2 አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር? 2 ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር?


跟着我们:

广告


广告