Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 23:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የማምለኪያ ዐፀድንም ጣዖት ከእግዚአብሔር ቤት ወደ ኢየሩሳሌም ውጭ ወደ ቄድሮን ፈፋ አወጣው፤ በቄድሮንም ፈፋ አጠገብ አቃጠለው፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ ትቢያውንም በሕዝብ መቃብር ላይ ጣለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የአሼራንም ምስል ዐምድ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አውጥቶ ከኢየሩሳሌም ውጭ ወዳለው ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ አቃጠለው፤ አድቅቆ ፈጭቶም በሕዝቡ መቃብር ላይ በተነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፥ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፥ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ጣዖት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ወደ ቄድ​ሮን ፈፋ አወ​ጣው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፥ ትቢ​ያ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ላይ ጨመ​ረው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 23:6
20 交叉引用  

እነርሱም ደግሞ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ቅጠሉ ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች መስገጃዎችንና ሐውልቶችን የማምለኪያ ዐፀዶችንም ለራሳቸው ሠሩ።


በማምለኪያ ዐፀድ ጣዖት ስለሠራች እናቱን መዓካን እቴጌ እንዳትሆን ሻራት፤ ጣዖትዋንም ሰበረው፤ በቄድሮንም ፈፋ አጠገብ አቃጠለው።


አክዓብም የማምለኪያ ዐፀድ ተከለ፤ አክዓብም ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያስቆጣውን ነገር አበዛ።


በወጣህበትም ቀን፥ የቄድሮንንም ፈፋ በተሻገርህበት ቀን ፈጽመህ እንድትሞት እወቅ፤ ደምህ በራስህ ላይ ይሆናል፤” አለው።


ከበኣልም ቤት ሐውልቶቹን አወጡ፤ አቃጠሉአቸውም።


የበኣልን ሐውልት ቀጠቀጡ፤ የበኣልንም ቤት አፈረሱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የውዳቂ መጣያ አደረጉት።


እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “በዚህ ቤት ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘላለም አኖራለሁ፤


የይሁዳም ነገሥታት ያሠሩትን በአካዝ ቤት ሰገነት ላይ የነበሩትን መሠዊያዎች፥ ምናሴም ያሠራውን በእግዚአብሔር ቤት በሁለቱ ወለሎች ላይ የነበሩትን መሠዊያዎች ንጉሡ አስፈረሳቸው፤ አደቀቃቸውም፤ ትቢያቸውንም በቄድሮን ፈፋ ጣለ።


ደግሞም በቤቴል የነበረውን መሠዊያ፥ እስራኤልንም ያሳተ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያሠራውን የኮረብታውን መስገጃ፥ ይህን መሠዊያና መስገጃ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹንም ሰባበረ፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ የማምለኪያ ዐፀዱንም አቃጠለው።


ንጉሡም አሳ እናቱን መዓካን በማምለኪያ ዐጸድ ጣዖት ስላደረገች ከእቴጌነትዋ አዋረዳት፤ አሳም ምስልዋን ቈርጦ ቀጠቀጠው፤ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው።


አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ ለበኣሊምም መሠዊያ ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።


የበኣሊምንም መሠዊያዎች በፊቱ አፈረሱ፤ በላዩም የነበሩትን የፀሐዩን ምስሎች የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የተቀረጹትንና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች ሰባበረ፤ አደቀቃቸውም፤ ይሠዉላቸው በነበሩት ሰዎች መቃብርም ላይ በተናቸው።


የሠሩትንም ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ ለእስራኤልም ልጆች አጠጣው።


ልጆቻቸውም ከለመለሙ ዛፎች በታችና በረዘሙት ኮረብቶች ላይ ያሉትን መሠዊያቸውንና የማምለኪያ ዐፀዳቸውን ያስባሉ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ጌታ ሆይ፥ ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም።


የሬሳም ሸለቆ ሁሉ የአመድም እርሻ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድረስ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፥ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘላለም አይነቀልም አይፈርስምም።


ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እነርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ።


የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።


ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወሰድሁ፥ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቀቅሁትም፥ እንደ ትቢያም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት፤ ትቢያውንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።


የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በኣሊምንና አስታሮትን አመለኩ።


跟着我们:

广告


广告